Friday, February 14, 2014

BREAKING NEWS : TAXI DRIVERS STRIKE IN ETHIOPIA

by MINILIK SALSAWI »



Imageየጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ መቱ

የጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ መምታታቸውን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡
የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንደጠቆሙት የተቃውሞው መነሻ ምክንያት ሶስት ተከታታ ቅታት የተጣለበት ሹፌር ለስድርት ወር እንዳያሽከረክር የሚከለክል ደንብ በመውጣቱ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓትም ሹፌሮቹ ጎንደር ፒያሳ ላይ ተሰብስበው አደባባዩን በክላክስ አድምቀውታል፡፡




በጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ እንደቀጠለ ነው:: የታክሲ ባለንብረቶችም የታሪፍ ማስተካከያ አለመደረጉን በመቃወም የታክሲ ሹፌሮቹን ተቀላቅለዋል፡፡ የከተማው አስተዳደር ባለስልጣናት ሾፌሮቹና ባለንብረቶቹ ወኪል ልከው እንዲነጋገሩ ጠይቀዋል፤ ሆኖም ሹፌሮቹ “የክልሉ መንግስት ወከሎችን በተደጋጋሚ የማሰር ልምድ ስላለው ወኪል አንልክም” ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment