
ከየካቲት 20/1966ቱ የሕዝባዊ ለውጥ በኋላ የተዩት እጅግ የሰለጠኑትና ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው የሰላማዊና የህጋዊ ታሪክ ባለቤት የሁኑት እንቅስቃሴዎች ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱም ቅዳሜ ሚያዝያ 12/1966 እና በሚያዚያ 30/1997 ከሰዓት በኋላ የተደረጉት ህጋዊ ሰላማዊ ሰልፎች ናቸው፡፡ የሚያዝያ 12ቱን ሰልፍ ያደረጉት ጨዋዎቹና አይበገሬዎቹ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ነበሩ፡፡ ከታላቁ አንዋር መስጊድ ተነስተው በቡድን በቡድን እየሆኑ በአትክልት ተራ አድርገው፣ በሲኒማ ኢትዮጵያ አልፈው፣ የልዑል ራስ መኮንንን ድልድይ ተሻግረው፣ አራት ኪሎ አደባባይ ደረሱ፡፡
... ከዚያም በታላቁ ቤተ-መንግስት በኩል አድርገው፣ በውጭ ጉዳይና በኢዮቤልዩ ቤተ-መንግስት በኩል ወርደው፣ መስቀል አደባባይን አለፉና፣ ወደ ለገሃር አቀኑ፡፡ በመቀጠልም ወደ ብሄራዊ ቴዓትር የሚወስደውን መንገድ ይዘው፣ የቴዎድሮስ አደባባይን ካለፉ በኋላ በመዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት እየዘመሩ ወደ አንዋር መስጊድ ተመለሱ፡፡ ሰላማዊ ሰልፉም ያላንዳች ሁከትና ረብሻ በሰላም ተጠናቀቀ (አዲስ ዘመን ጋዜጣ 13/1966 ገፅ 1 እና 2)፡፡
No comments:
Post a Comment