
ማህበረሰቡን በነፃነት ከማገልገል ይልቅ በዙርያቸው ካካበቧቸው ተቀናቃኞቻቸው በግብግብ ጊዜ የባከነባቸው አቶ ዘነበ ወደ ኩዌት እንደሚሄዱ ይነገራል።ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው ይቀጣሉ የሚል መላምትም አለ።
ከሳቸው ቀድመው የነበሩት አምባሳደር መርዋን በድሪን ያባረሩት የጊቢው ቢሮክራቶች በሁለተኛው ሙከራቸው እኚህን ሰው በመመንገላቸው ደስተኞች ሆነዋል።
አቶ ዘነበ በጅዳ ማህበረሰብ የሰሯቸው ስህተቶች የማይረሱ ቢሆንም÷ቆንስላ ጊቢ የተንሰራፋውን ሙሰኛነት ለመፋ...ለም ባደረጉት ጥረታቸው አይረሱም።
በኢሕአዴግ የመሰረታዊ ድርጅት ሠዎች ጥርስ የገቡት እኚህ ሰው መቋቋም ከማይችሏቸው በርካቶች የተያያዙት ትግል ተሸናፊ አድርጓቸው የአገልግሎት ዘመናቸው ከማብቃቱ በፊት የጅዳ ቢሮዋቸውን ሊለቁ ተገደዋል።
የጅዳ ኮሚዩኒቲ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት የወላጆች ስብሰባ ላይ ባለፈው ሐሙስ ምሽት በኮሚዩኒቲው ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ አሊ ሲወደሱ የነበሩት አቶ ዘነበ እጅግ አደገኛ የቢሮክራሲና ሙስና እምብርት የሆነውን ቆንስላ በቅርብ ቀን ይሰናበታሉ።
የጅዳ ኢትዮጵያዊን መሰረታዊ ፍላጎት ከማሟላት በላይ በብሔር ተቦዳድነው የየግል አጀንዳቸውን የሚፈፅም አገልጋይ የቆንስላ ባለሥልጣን የሚፈልጉት የድርጅት ሰዎች በአምባሳደር መርዋን የጀመሩት በሴራ ማባራር÷በአቶ ዘነበ መደገሙ ከአሁን ወዲያ ለሚሾሙት አምባሳደሮች የሚፈጥረው ተፅእኖ እንደሚኖር ይገመታል።
ከአሁን ወዲያ በቆንስላው ተሹመው የሚመጡ ባለሥልጣኖች ግንኙነታቸውን ቀጥታ ከህዝቡ ማድረጋቸው ኋላ ላይ እራሳቸውን ጠርጎ ከሚጠፋ አደጋ እንደሚታደጋቸው ከሁለቱ አምባሳደሮች ትምህርት መውሰድ አለባቸው።
የፖለቲካ ድርጅት አባላት በሚሰጧቸው የተሣሣተ ንድፍ በመጓዝ መውደቂያቸውን ከመግቢያ እንዳያነጥፉ መጠንቀቅ ያስፈልጋቸዋል ።
አቶ ዘነበ ከበደ ቀጣዩ የስራ ዘመናቸው መልካም እንዲሆንላቸው እንመኛለን ።
No comments:
Post a Comment