Thursday, February 27, 2014

በአዲስ አበባ ራሱን ያጠፋው የ24 ዓመቱ የጥበቃ ሠራተኛ ከኪሱ ደብዳቤ ተገኘ

bole


ባለፈው የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም በቦሌ አካባቢ አንድ የጥበቃ ሠራተኛ 3 ጊዜ ጥይት ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን እንዳጠፋ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ ዘግበን፤ ለምን ራሱን ሊያጠፋ እንደቻለ የሚገልጽ መረጃ አለመገኘቱን ዘግበን ነበር። በአዲስ አበባ ከተማ ታትሞ የሚወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ እንደገለጸው ሟች በሱፈቃድ በጋሻው ራሱን ለማጥፋት የወሰነበት ደብዳቤ በኪሱ ተገኝቷል፤ ሲል ዘግቧል። ሟች ጊዜውን ባይጠቅሰውም በተወለደበት አካባቢ ነዳጅ የጫነ ተሳቢ ፍሬን ተበጥሶ ከሞት ማምለጡን፣ መሞት ካለበት ደግሞ ራሱን በራሱ ማጥፋት እንዳለበት መወሰኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ጽፎ በኪሱ መገኘቱ ተዘግቧል።
የሪፖርተር ዘገባ እንደወረደ፦
ወጣቱ የጥበቃ ሠራተኛ በሱፈቃድ በጋሻው በኪሱ ውስጥ ከተገኙት የተለያዩ መታወቂያዎች መረዳት እንደተቻለው፣ አጋር የጥበቃ ሠራተኞች ማሠልጠኛ ተቋም ተቀጣሪ ነው፡፡ በተጨማሪም የኮሌጅ ተማሪ መሆኑን በሚገልጸው መታወቂያ ላይ እንደሠፈረው ከሆነ፣ በ1982 ዓ.ም. የተወለደና የ24 ዓመት ወጣት ነው፡፡ በምን ምክንያት ከፖሊስ ባልደረባነት እንደለቀቀ ባይታወቅም፣ የ13ኛ ኮርስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባል እንደነበር በቅርብ ከሚያውቁት ወዳጆቹ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በባንኩ አሠራር አንድ የጥበቃ አባል 24 ሰዓት ሠርቶ 24 ሰዓታት የሚያርፍ በመሆኑ፣ ሟች በሱፈቃድም የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት አዳሪ ጓደኛውን ከቀየረ በኋላ፣ ባንኩን ለመጠበቅ የቻለው ለ24 ሰዓታት ሳይሆን ለሰባት ሰዓታት ብቻ ነው፡፡ ወጣቱ ‹‹ኑሮ መሮኛል›› በማለት እያማረረ እያለ በመሀል የያዘውን ጠመንጃ ቃታ በመሳብ አንድ ጊዜ ወደ ላይ ሲተኩስ፣ አብረውት የነበሩ ሴት ፈታሽና ሌሎች የባንኩ ተጠቃሚዎች በመደናገጥ ወደ ውስጥና ወደ ውጭ ሽሽት ይጀምራሉ፡፡ ሁለተኛውን ጥይት በመተኮስ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ በኩል በፍጥነት መራመድ መቀጠሉን በሥፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
ሦስተኛውን ጥይት ወደ ላይ ከተኮሰ በኋላ አራተኛውን አንገቱ ሥር በመደገን ተኩሶ፣ ራሱን ማጥፋቱን የዓይን እማኞቹ አስረድተዋል፡፡
ሟች በሱፈቃድ ተወልዶ ያደገው በጉለሌ አካባቢ እንደሆነ፣ አሁንም ከቤተሰቡ ጋር እየኖረ እንደሚገኝ፣ ጊዜውን ባይጠቅሰውም በተወለደበት አካባቢ ነዳጅ የጫነ ተሳቢ ፍሬን ተበጥሶ ከሞት ማምለጡን፣ መሞት ካለበት ደግሞ ራሱን በራሱ ማጥፋት እንዳለበት መወሰኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ጽፎ በኪሱ መገኘቱም ተሰምቷል፡፡

Tuesday, February 25, 2014

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ ለማዳከም አፋኝ ሕጎችን ይጠቀማሉ፤ግለሰቦችንም ፖለቲካዊ መነሾ ያላቸውን ክሶች በመመስረት የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ።ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ ለማዳከም አፋኝ ሕጎችን ይጠቀማሉ፤ግለሰቦችንም ፖለቲካዊ መነሾ ያላቸውን ክሶች በመመስረት የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ።
የስዊስ አቃቢ ህግ የረዳት ሃይለመድህን አበራን ሰብአዊ መብቶች ያከብራል ሲሉ ቃል አቀባዩዋ ተናገሩ
--------------------------------------------------------------------------------------
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰዊስ አቃቢ ህግ ቃል አቀባይ ሚስ ያኔት ባልመር በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ የምርመራ ሂደቱ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ዝርዝር መረጃዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ገልጸው፣ የሰብአዊ መብቱን በመጠበቅ በኩል ለተነሳው ጥያቄ ግን ስዊዘርላንድ የሰብአዊ መብቶችን በጠበቅ በኩል ታዋቂ አገር መሆኑዋን በመግለጽ የሃይለመድህንን የሰብአዊ መብቶች እንደሚያከብሩ ገልጸዋል።
ሃይለመድህን ጠበቃ ተቀጥሮለት ጉዳዩን በመከታተል ላይ ነው...። የሃይለመድህንን የፍርድ ቤት ጉዳይ መከታተል ይቻል እንደሆን የተጠየቁት ቃል ሚስ በርነር፣ በአሁኑ ሰአት ስለፍርድ ቤት ሂደት ለማውራት ባይቻልም በስዊዘርላንድ አብዛኛውን ጊዜ ፍርድ ቤቶች በግልጽ ችሎት ጉዳዮችን እንደሚያዩ ተናግረዋል።
የሚቀጥለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቀን ይታወቅ እንደሆን ሲጠየቁም ” እዛ ደረጃ ላይ ገና አልተደረሰም” በማለት መልሰዋል። የምርምራው ሂደት መቼ እንደሚጠናቀቅ ሲጠየቁም፣ የስዊስ የፍትህ አሰራር መረጃዎችን በሚስጢር መያዝን ስለሚያዝ፣ ምንም አይነት መግለጫ መስጠት እንደማይቻል አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ስዊዘርላንድ ለረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጥገኝነት እንደትሰጥ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 28 በበርን እንደሚካሄድ በስዊዘርላንድ የ ዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ የስውዘርላንድ የድጋፍ ኮሚቴ ገልጿል።

የአቃቤ ህጉ የሀሰት መስካሪዎች የሰጡት የምስክር ቃል

ድምጻችን ይሰማ፡በደሴ
የአቃቤ ህጉ የሀሰት መስካሪዎች የሰጡት የምስክር ቃል

ክፍል -1
...See More

በጭካኔ እየተገዳደልን፣ ወዴት እየሔድን ነው?


የአብዱ ሁሴን ይማም ግድያ
http://www.goolgule.com/killing-each-other-and-where-to/

ከሳምንት በፊት እዚህ ጅዳ ሻረ ሄራ በሚባል አካባቢ የሃበሻን ዘር ያሳዘነ የግድያ ድርጊት መፈጸሙን ሰማሁ። ትውውቅ ባይኖረንም በአይን የማውቀው ወንድም አብዱ ሁሴን ይማም በጭካኔ መገደሉን የሰማሁት ድርጊቱ በተፈጸመ ከሰአታት በኋላ ከአንድ ወዳጀ በኩል በደረሰኝ የስልክ መልዕክት ነበር። በቀጣይ ቀናት ወጣቱ አብዱ የተቀጠፈበትን የጭካኔ ድርጊት የሚያወግዙ በርካታ መልዕክቶች ማስተናገድ ጀመርኩ። በመካከላችን ባሉ ጥቂት የሰው አውሬዎች እየሆነ ያለው እና ስማችን የመክፋቱ ነገር ያሳሰባቸው በርካታ ወገኖች በግድያው ማዘናቸውን በመግለጽ በርካታ መልዕክቶችን ልከውልኛል። በጭካኔ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት ዘልቆ ነፍሱን አስጨንቆ ያሳዘነው አንድ ወንድም የላከልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል ….

“ጩኸት ሰሚ ሲያጣ እንዴት ያናዳል … ሀበሻ የድሮዎቹ የሉም … ውድ የሆነውን የሰውን ደም በከንቱ የሚጠጡ እርኩስ መንፈስ የተጠናውታቸው ውሾች ናቸው … ሰሞኑን በ ጅዳ አካባቢ ሸር ሄራ አካባቢ የተደረገውን ግፍ ልንገርህ … በሀበሾች ጭካኔ የተገደለውን ልጅ በአካል አውቀዋለሁ አብዱ ሁሴን ይማም ይባላል … በሳንጃ ገደሉት! ልብ በል … የሳውድ መንግስት ታዲያ እንዴት አያሳድደን! እንደነዚህ አይነት እርኩሶች እያሉ እኛ ቤተሰብ እንዴት እንርዳ? ልጅስ እንዴት እናስተምር? .. ነብዩ ሰው እንዴት … የሰውን ነፍስ ያጠፋል? ደግሞም ሳውዲ ውስጥ? ከተሰራ ለሚገኝ ገንዘብ እጅግ ያሳዝናል ይጎመዝዛል! ጌታ እውነቱን ይፍረድ ለሀበሻ ጩኸት በቃኝ እኔም ሀበሻ ነኝ!!!” ይላል!

ሰሞኑን “ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊ ላይ በግፍ የግድያ ወንጀል ተፈጸመ!” የሚለው ወሬ ከጓዳ እስከ አደባባይ ሲናኝ አስከፊውን ሂደት የታዘቡ ወገኖች ኢትዮጵያውያን ብቻ አልነበሩም። ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁና ከሚከታተሉ የሃገሩ ሰዎችም መልዕክቶችና አስተያየቶች ደርሰውኝ በሃፍረትም ቢሆን ለማስተናገድ ተገድጀም ነበር … የሟችን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉ፣ ኢትዮጵያን የሚወዱና ስለኢትዮጵያ የሚጽፉ፣ አንድ ከፍ ያለ ሃላፊነት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያና ሃያሲ የሃገሩ ሰው አዝነውብን አግኝቻቸዋለሁ። በቁም ነገር በቢሯች አስጠርተው ያሉኝ እንዲህ ነበር “ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ምንድ ነው እንዲህ የመሰለ የዘቀጠ በሃበሾች ያልተለመደ ጉዳይ ተደጋገመሳ? ሀበሾች ምን ገባባችሁ? ከአመታት በፊት በሪያድ መንፉሃ ፣ ከወራት በፊት በመዲና በአብሃ እና በዙሪያው ያን ሰሞን ደግሞ በኪሎ ተማንያ እና በዙሪያው በሃበሾች መካከል መጨካከን የተሞላበት ድርጊት ታይቷል። ከሁሉም የሚያሳዝነው የግድያ ምክንያቶቹ ጊዜያዊ ጸብን ፣ ጥቅምንና ጥቃቅን የሰው ህይዎትን በጭካኔ ሊያስጠፉ የማይገባቸው ምክንያቶች ናቸው። ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው?” ሲሉ በጥያቄ ላፋጠጡኝ ሳውዲ ወዳጀ የሚሆን መልስ ግን አልነበረኝም! ብቻ የሆነው አሳዝኖ ፣ አሳፍሮ አንገቴን አሰበረኝ …

እርግጥ ነው፣ ባሳለፍናቸው አመታት በሪያድ መንፉአ አካባቢ አልፎ አልፎም በኢትዮጵያውያኑ መካከል በሚፈጠር ግጭት ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ዜጎች በሰላ ጩቤ አሰቃቂ ጥቃት ተፈጽሞባቸው የመቁሰልና የመገደል አደጋ ምክንያት እንደ ነበር የአይን እማኞች አጫውተውኝ ነበር። በጩቤ ለመወጋጋቱ ዋንኛ ምክንያትም ደግሞ ተራ ከገንዘብና ከሴት ጋር የተያያዙ እዚህ ግቡ የማይባሉ መሆናቸው ማጤንና መገንዘብ ደግሞ በእጅጉ ያሳዝናል … በቀደሙት ጥቂት አመታት በሳውዲና የመን ድንበር ከተሞች ይህ መሰሉ ወንጀል የከፋ እንደ ነበር አውቃለሁ። በተለይም በጀዛን፣ በአብሃና በከሚስ ምሽት በሚባሉ አካባቢዎች በዙሪያው ባሉ የከተማና የገጠር ከተሞች በከተሙ ኢትዮጵያውያን መካከል ተፈጸሞ የምንሰማው ግድያ ፍጹም ጭካኔ ያልተለየው መሆኑ ይጠቀሳል ! ወደ አብሃና ከሚስ ምሸት ለስራ ባቀናሁባቸው ቀናት በእኛ ዙሪያ እየሆነ ያለውን ለመስማት የከበደ መረጃ በእጀ መድረሱን አስታውሳለሁ። በህገ ወጥ መንገድ ዜጎቻችን ከየመን ሳውዲ በሚያመላልሱ ለገንዘብ በገንዘብ እየሸጡ የሚተዳደሩ ደላሎችና አቀባባዮች በጎሳ ተቧድነውና ብሔርን ለይተው የሚከሰተውን ግጭት ከጩቤ ያለፈ እንደ ነበርም በቦታው ተገኝቸ ታዝቤያለሁ። በተለይም በአብሃ አካባቢ በግጭቱ ስለተቀጠፈው ህይዎት ፣ ፍርድን ይጠባበቁ ስለነበሩ የእኛ ገዳዮችም የፍርድ ሂደት በቅርብ እከታተል ነበር። ከሁሉም የሚያሳዝነው የሰውን ልጅ ያህል ታላቅ ፍጡር በስለት የሚጠፋበትን ምክንያት መስማት እንደ ነበርም ትዝ ይለኛል። ከሃገር ቤት ያለ የዘር ፣ የግል ጥላቻና ጸብን መሰረት ያደረገው የደም መቃባት ፣ በገንዘብ መካካድ “ጓደኛየን ነጠቀኝ!”፣ “የሰማንያ ሚስቴን ደፈረ !”፣ በሚሉትና በመሳሰሉት ክሶች የሚያጠነጥነው ብቀላ በፍትህ ሳይሆን በጭካኔ ለመወጣት የሚፈጸም ያረጀ ያፈጀ ይትበሃል ሳውዲ ተከትሎን መጥቶ ስማችን ማርከሱ ደግሞ ከሁሉም በላይ ያማል!

በያዝነው አመት ከጅዳ በ400 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው በሙስሊማን ቅዱስ ከተማ በመዲናም በዜጎቻች መካከል በተፈጠረ የቨዛ ሽያጭ እና ተጓዳኝ የገንዘብ መካካድ ያስከተለው አምባጓሮ በቅዱሷ ከተማ ቅዱስ የማይባል ግድያ ለመፈጸሙ ምክንያት ነበር። ይህም የጭካኔ ወንጀል የተፈጸመበት ኢትዮጵያዊ ፣ ወንጀል ፈጻሚው ኢትዮጵያዊው መሆኑ ደግሞ ጉድ አሰኝቶ አሳፍሮን አልፏል። ከወራት በፊትም እዚሁ ጅዳ በተለያዩ አካባቢዎች በኢትዮጵያውያን መካከል የተነሱ አምባጓሮዎች በተመሳሳይ ጭካኔ በተሞላባቸው የግድያ ድርጊቶች የተከበቡ ወንጀሎች ምክንያት ነበሩ ማለት ይቻላል። እናም ጉዳዩ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል ….

ባሳለፍነው ሳምንት በጭካኔ የተገደለው ወንድም ወንጀል ተጠርጣሪ፣ ተጠያቂ የቅርብ ጓደኛ ወዳጁ እንደነበረና ከቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ሰማን ! አብዱ በማጣታቸው ትልቁ የሃዘን መርግ የወደቀባቸው፣ የሚይዙት የሚጨብጡ ያጡት፣ ቤታቸው የጨለመባቸው አንዲት ሴት ልጂና የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱ ሃዘን የከበደ ነው… ስለአብዱን ቅንነት፣ ሰው አማኝ ፣ ትጉህና ታታሪነቱን የሚመሰክሩት ባልንጀሮቹም ሃዘናቸው መሪር ያደረገው የተፈጸመው የጭካኔ ወንጀል ብቻ ሳይሆን የወንጀሉ ቀዳሚ ተጠርጣሪ የቅርብ ወዳኛ መሆኑ ነበር። በዚህም ሊያምኑት በከበደ ድርጊት እርር ድብን ብለው አዝነዋል! ዛሬ የማይሰማ የማያየን አብዱ ሁሴን በሰላሳዎቹ የእድሜ ክልል ይገኝ እንደነበር በቅርብ ጓኞቹ ጨምረው አጫውተውኛል ። የወንድም አብዱ ሁሴን ይማም የቀብር ስነ-ስርዓት ትናንት የካቲት 12/ 2006 ረቡዕ ከቀትር በኋላ በጅዳ ከተማ ተፈጽሟል! አብዱ የሔደው ሁላችንም ወደ ማንቀርበት የላይኛው ቤት ነው! ነፍሱን ይማረው ! “አላህ ይርሃሙ!”

ወንጀሉን በትኩሱ ለማቅረብ በፖሊስ ክትትክ መሆኑና ተጠርጣሪ ወንጀለኛው ባለመያዙ የማለዳ ወጌን እንዳዘገየው ቢያስገድደኝም መረጃውን ባሳለፍናቸው ቀናት ከበርካታ ነዋሪዎች አስተያየቶችን ለመሰብሰብ ሞክሬ ነበር። በዚህ መሰል ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ዙሪያ እየተነጋገረ የሚገኘውን አብዛኛው የጅዳ ነዋሪ “ህጋዊ ህገ ወጥ” ነገን ምን ይከተል ይሆን እያለ በጭንቀት በሰቀቀን እየጠበቀ ባለበት ሰአት የዚህ መሰሉ ድርጊት መፈጸም “እንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ!” ሆኖበት ተመልክቻለሁ! ለእኔም የሆነብኝ እንዲያ ነው …

ድርጊቱ አሳዝኖኝ ለማውገዝ ያነሳሁት ብዕር መቋጫ የሚሆነው ሳውዲው ሃያሲ ወዳጀ ያጫወቱኝን ዘልቆ የሚሰማ ያልመለስኩት ጥያቄ ነው። ሃያሲው ሃበሾች በዚህ መሰል ድርጊት እንደማንታወቅ ተናትነው ከቅርብ አመታት የሰበሰቧቸው መረጃዎች ቢያሳስቧቸው ቆጣ ብለው በንዴት ሲያጠይቁ “ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው? “ ነበር ያሉኝ …እኔም ተጠርተን የማናውቅበት ወንጀል ሲደጋገም አሞኛልና ድርጊቱን አወግዘዋለሁ! ወደ መጨረሻም አሳፍሮ መልስ ያጣሁለትን የሃያሲውን ወዳጀ ጥያቄ ላጠይቅ ግድ አለኝ … ግንስ … በጭካኔ እየተገዳደልን ፣ እየተጠላላን ወዴት እየሔድን ነው? ምንድን ነው እየሆነ ያለው?

ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
Like ·  ·  · 

Monday, February 24, 2014


“ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል።” ጄኔራል ሳሞራ የኑስ


ከሳምንታት በፊት ራሱን የአማራ ክልል ብሎ በሚጠራው የክልል አምባገነን ጁንታ አስተዳዳሪ ነኝ የሚለው የብኣዴን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አለምነህ መኮንን በድርጅቱ የውይይት መድረክ ላይ የአማራውን ህዝብ ለሃጫም እና ልጋጋም እንዲሁም መርዝ ብሎ መሳደቡን ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ የውጪ እና የውስጥ ተቃውሞ በየአቅጣጫው እየተነሱ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል::
ሰሞኑን በብአዴን አመራሮች እና በካድሬዎቻቸው መካከል ግለሰቡን የተመለከተ አለመግባባት መከሰቱን እና ጥያቄዎች ከአባላቱ በስፋት እየመጡ መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ጠቅሰው የአዲስ አበባ እና አከባቢው የድርጅቱ ካድሬዎች ግለሰቡ እና ሁኔታው እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል እስከማለት ደርሰዋል:: ይህንን ለመናገር የፈለገው ለምንድን ነው ተልእኮውስ ምንድነው? በሌላው ብሄር ላይ ይህ ነገር ቢነገር የድርጅታችን እርምጃ ምን ይሆን ነበር? ግለሰቡ በህግ ሊጠየቅ ይገባል::የሚሉ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተጠየቁ ቢሆንም አመራሮቹ እስካሁን መልስ ከመስጠት ይልቅ ኢዲሞክራሲይዊ በሆነ መንገድ አለመግባባቶችን ከመፍታት ይልቅ በማስፋት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ጸረ-… እያሉ ጠያቄዎችን በመወንጀል እና ዋናውን ክትትላቸው ያደረጉት ድምጹን ቀድቶ ማን አውጣው የሚለውን የማይመለስ ጥያቄ ይዘው አደና ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል::
ከድርጅቱ አንዳንድ ካድሬዎች እንደሚሰማው የድምጹን ቅጂ ያወጡት የሕወሓት ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ እና ሕወሓትን በጥርጣሬ የሚይስቡ እንዲሁም ግንቦት ሰባት ናችሁ ብለው እርምጃ ሊወስዱባቸው የሚፈልጉትን የብኣዴን ካድሬዎች ለመዋጥ የተደረገ ሴራ ነው::በድርጅታችን ውስጥ የማይበጁትን አንጠባጥቦ የራሱን ለመሰግሰግ ያሰረው ሕወሓት መንገድ አገኘ ቢሉም በለላ ወገን ደግሞ በድርጅቱ የተማረሩ እና የለውጥ ፍላጎት ያላቸው የብአደን አመራሮች አሹልከው ያወጡት እንደሆነ ይነገራል።ካድሬዎቹ ክፉና ደጉን እንድንለይ ላደረገን ኢሳት ቴሌቭዥን ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ ተደምጠዋል:: በአመራሮቹ እና በካድሬዎቹ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በዚሁ ከቀጠለ አቶ አለምነህ የድርጅት ስራ ብቻ እንዲሰሩ ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት እና በክልሉ ላይ የተሰጣቸውን ስልጣን ለስም ብቻ እንዲቀመጥ የሚደረግ እንደሚሆን እና ቀስ በቀስ ከድርጅቱ ገፍቶ በማስወጣት አምባሳደር አድርጎ መሾም የሚሉ አስተያየቶች ከድርጅቱ አከባቢ ተደምጠዋል::ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የብሄር ተዋፅኦን እና የመኮንኖች ቅነሳን በተመለከተ ከፍተኛ የሆነ ክርክር መነሳቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል:: እንደምንጮቹ ከሆነ በዚህ ሰሞን በተካሄዱ ተከታታይ ምስጢራዊ ስብሰባዎች ላይ የመከላከያ ሰራዊቱ በአንድ ብሄር በተሰበሰቡ ጄኔራሎች የተሞላ ነው: የመኮንኖች ቅነሳ ለምን አስፈለገ? ለምንስ አማራው እና ኦሮሞው ላይ አተኮረ ?ሰራዊቱ እና ቤተሰቡ በኑሮ ውድነት እየዋተተ ነው ከፍተኛ መኮንኖች በሙስና ተዘፍቀዋል ህገመንግስቱ አልተተገበረም የሚሉ የህዝብ አቤቱታዎች ተበራክተዋል … የሚሉ በሰራዊቱ ውስጥ ተጠንቷል ተብለው በቀረቡ ጥያቄዎች ዙሪያ ክርክር እና ውይይት የተደረጉ ቢሆንም በሕወሓት ጄኔራሎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንዲሁም ሞራልም ያልጠበቁ ስድቦች ካለውጤት እንደተበተኑ ምንጭኦቹ ገልጸዋል::
የአንድ ብሄር የበላይነት የምትሉት ለሕወሓት ያላችሁን ጥላቻ ለመግለጽ ነው ያሉት ጄኔራል ሳሞራ ጥያቄውን የፓርቲ ስብሰባ እስኪመስል ድረስ ጮኽውበታል::በትግል የከፈልነው መስዋትነት ውጤት እንጂ ከጎዳና ላይ መጥተን ማእረግ አልተሰጠንም::ከየብሄሩ አስፈላጊ ያልነውን ሊሰራልን የሚችለውን ጄኔራል እያደረግን እየሾምን ነው:: ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል። ሲሉ በመከላለያ ኢንዱስትሪ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ጠና ላይ ተሳልቀውባቸዋል::
የሰራዊቱ መኮንኖችን ቅነሳ በተመለከተ የማይታጠፍ እቅድ ስለሆነ ተግብርዊ ይሆናል ያሉት ሳሞራ ብሄር ለይተን ያደረግነው ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና የመከላከያ ሰራዊቱ ተጠንቶ የሚወሰድ ኢርምጃ ነው ብለዋል::ለሰራዊቱ የምናደርገው ድጎማ የለም::ያልተመቸው ካለ ሰራዊቱን መሰናበት ይሽላል ሲሉ በቁጣ የመለሱ ሲሆን ሙስና የሚባለው ማስረጃ ያለው ሄዶ ሊከስ ይሽላል ከዚህ ውጭእ ስም ማጥፋት ነው ሲሉ ተደምጠዋል :;ህገመንግስቱን እና መንግስታዊ ስርኣትን በተመለከተ መልካም አስተዳደር እና ልማት ስለሰፈነ ቢዚህ ልይ ምተኮር ስፈላጊ አይደለም ብለዋል:: ከሰራዊቱ አባልት መሃል ገብተን ያስጠናነው ጥያቄ ነው እየተወይየንበት ያሉትን ሰነድ በተመለከተ ማንም የጦር መኮንን አስተያየት ያልሰጠበት እና ያልጠየቀ ሲሆን ሁሉም በዝምታ በማዳመጥ ሳይወያይ መስማማት አለመስማማቱን ሳይገልጽ የተነገረውን እንደ መመሪያ ተቀብሎት መውጣቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::

ሰበር ዜና!!!
የመስጊድ ኢማሞች የሚሾሙት በመንግስት በራሱ መሆኑን መንግስት አመነ!!!
ሕዝቡ ሳያውቀው ሕገ መንግስቱ ተቀይሮ ይሆን? ...
ሰኞ የካቲት 17/2006

መንግስት ‹‹እኔ በሾምኳቸው የመስጊድ ኢማሞች (አሰጋጆች) አልሰገዳችሁም›› በሚል ንጹሀን ሙስሊም ግለሰቦች ላይ ክስ ያቀረበበት ሰነድ ተገኘ!!!

ከፍርድ ቤት የውስጥ ምንጮቻችን የተገኘውና በፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሀን አለባቸው ፊርማ በታህሳስ 4/2006 የተጻፈው ይኸው የክስ ሰነድ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ የቀረበ ሲሆን ሁለት መስጂድ ውስጥ በኢማምነት ያሰገዱ ሙስሊም ግለሰቦችንም ተከሳሽ አድርጎ አቅርቧል፡፡

ሰነዱ እጅግ አስገራሚውን ክስ ሲያብራራ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ በቁባ መስጂድ የአህባሽ ተከታዩን ኢማም ተከትሎ ለመስገድ ፍቃደኛ ያልሆነውን ህዝበ ሙስሊም ማሰገዳቸውንና በዚህ ተግባራቸውም ‹‹የሃይማኖት ሰላም ስሜት›› መንካታቸውን ገልጿል፡፡ ቃል በቃልም ሁለተኛ ተከሳሽ ‹‹መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም ሳይፈቀድለት የእነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊው ሙስሊም እንዳይሰግድ በማድረግ...›› ወንጀል መስራቱን ገልጿል፡፡

እስካሁን ‹‹መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ መንግስታዊ መርህ አልጣስኩም›› እያለ ሲከራከር የቆየው መንግስት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲጋለጥ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን መከራከሩ እንደማያዋጣው አውቆ በማን አለብኝነት ‹‹እኔ የሾምኩትን ኢማም አልተከተላችሁም›› በሚል ፍርድ ቤት ችሎት ማሰየም መጀመሩ ‹‹ህገ መንግስቱ አንድ ቀን ይከበር ይሆናል›› ለሚሉ ወገኖች ትልቅ መርዶ ይዞ መጥቷል፡፡ የአገሪቱ ‹‹የፍትህ›› አካላት የሆኑት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች መንግስት የሾመውን ኢማም ተከትላችሁ አልሰገዳችሁም›› በሚል ኢ-ህገ መንግስታዊ ክስ ላይ በይፋ መሰየማቸውም ለሀገሪቱ የፍትህ ስርአት የቁልቁለት አዘቅት መሆኑ አያጠራጥርም!

ህዝበ ሙስሊሙ ከ1987 ጀምሮ በመንግስት ሹመኞች ቁጥጥር ስር የዋለውን መጅሊስ ተቀባይነት የነሳውና ለመሪ ተቋሙ መመለስም እስካሁን እየታገለ ያለው መጅሊሱ የመንግስት ካድሬዎች መጫወቻ በመሆኑ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በመጅሊሱ ስም የሚካሄዱት ሁሉም ተግባራት በመንግስት የሚሾፈሩ መሆናቸውም የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ቆይቷል፡፡ የዛሬውን ዜና ልዩ የሚያደርገው ግን መንግስት ‹‹ሽብርተኝነት›› እና ሌሎች የማስመሰያ ስሞች ሳያስፈልጉት ‹‹እኔ የመረጥኩልህን እምነት አልተከተልክም፤ እኔ በሾምኩልህ ኢማም አልሰገድክም›› ሲል በግልጽ በሰነድ ጭምር ምስክር ጠርቶ ችሎት ፊት ሰዎችን ማቆሙ ነው፡፡ ይህም ይፋ መውጣቱ መንግስት የደረሰበትን የሃይማኖታዊ አፈና ደረጃ ለመላው ዓለምና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት ይበልጥ ይፋ የሚያደርግ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡

አዎን! የመንግስት ሃይማኖታዊ ጭቆና በምንም መልኩ መደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ግን ከሁለት አመታት በላይ ኢ-ፍትሀዊነትን ሲታገል የቆየው ህዝበ ሙስሊም የበለጠ በትግሉ ላይ እንዲጠናከር የሚያደርገው እንጂ ተስፋ የሚያስቆርጠው አይደለም፤ ህዝብ ተስፋ አይቆርጥም! ህዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖት ነጻነቱ እስኪከበርና የዜግነት መብቱን የሚጋፉ አሰራሮች እስኪቀረፉ ድረስ በጽናት መታገሉን ይቀጥላል፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!!!

ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

Like ☑ Comment ☑ Share ☑

ይህኛውን ሊንክ ጠቅ በማድረግ መደበኛውን ድረ ገጻችንን መጎብኘት ይችላሉ!
http://www.dimtsachinyisema.info

ይሄን ሊንክ ጠቅ አድርገው ይከተሉና አዲሱን የፌስቡክ
በዋሽንግተን ዲሲ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለረዳት አብራሪ ሃይለመድህን ድጋፋቸውን እየገለጹ ነ

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በሚያምር እና በደመቀ መልኩ ሁኔታ እየተደረገ ነው ። በአመሪካ የሲዊዘርላንድ አንባሳደር ከኤምባሲው በመውጣት ከኢትዮጵያውያኑ ጋር በመቀላቀል "....እናውቃለን በኢትዮጵያ ምን እንደሚደረግ ..." በማለት ግንዛበያቸውን የገለጹ ሲሆን ለኤንባሲው አምባሳደር ደብዳቤውን ሰልፈኛው አስረክቧል። የመጣው ሰልፈኛ በርካት ሲሆን እናቶች ህፃናት ሳይቀሩ ሰላማዊው ሰልፍ ላይ መገኝታቸው የሚያስደስት ሁኔታ ነው።

video 20140221 627629


ETHIOPIAN MUSLIMS WEEDING HISTORICAL (BBN RADIO) ታሪካዋው ሰርግ ቢቢኤን ልዩ ዘገባ...


ድምፃችን ይሰማ

ሰበር ዜና!!!
የመስጊድ ኢማሞች የሚሾሙት በመንግስት በራሱ መሆኑን መንግስት አመነ!!!...
ሕዝቡ ሳያውቀው ሕገ መንግስቱ ተቀይሮ ይሆን?
ሰኞ የካቲት 17/2006

መንግስት ‹‹እኔ በሾምኳቸው የመስጊድ ኢማሞች (አሰጋጆች) አልሰገዳችሁም›› በሚል ንጹሀን ሙስሊም ግለሰቦች ላይ ክስ ያቀረበበት ሰነድ ተገኘ!!!

ከፍርድ ቤት የውስጥ ምንጮቻችን የተገኘውና በፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሀን አለባቸው ፊርማ በታህሳስ 4/2006 የተጻፈው ይኸው የክስ ሰነድ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ የቀረበ ሲሆን ሁለት መስጂድ ውስጥ በኢማምነት ያሰገዱ ሙስሊም ግለሰቦችንም ተከሳሽ አድርጎ አቅርቧል፡፡

ሰነዱ እጅግ አስገራሚውን ክስ ሲያብራራ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ በቁባ መስጂድ የአህባሽ ተከታዩን ኢማም ተከትሎ ለመስገድ ፍቃደኛ ያልሆነውን ህዝበ ሙስሊም ማሰገዳቸውንና በዚህ ተግባራቸውም ‹‹የሃይማኖት ሰላም ስሜት›› መንካታቸውን ገልጿል፡፡ ቃል በቃልም ሁለተኛ ተከሳሽ ‹‹መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም ሳይፈቀድለት የእነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊው ሙስሊም እንዳይሰግድ በማድረግ...›› ወንጀል መስራቱን ገልጿል፡፡

እስካሁን ‹‹መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ መንግስታዊ መርህ አልጣስኩም›› እያለ ሲከራከር የቆየው መንግስት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲጋለጥ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን መከራከሩ እንደማያዋጣው አውቆ በማን አለብኝነት ‹‹እኔ የሾምኩትን ኢማም አልተከተላችሁም›› በሚል ፍርድ ቤት ችሎት ማሰየም መጀመሩ ‹‹ህገ መንግስቱ አንድ ቀን ይከበር ይሆናል›› ለሚሉ ወገኖች ትልቅ መርዶ ይዞ መጥቷል፡፡ የአገሪቱ ‹‹የፍትህ›› አካላት የሆኑት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች መንግስት የሾመውን ኢማም ተከትላችሁ አልሰገዳችሁም›› በሚል ኢ-ህገ መንግስታዊ ክስ ላይ በይፋ መሰየማቸውም ለሀገሪቱ የፍትህ ስርአት የቁልቁለት አዘቅት መሆኑ አያጠራጥርም!

ህዝበ ሙስሊሙ ከ1987 ጀምሮ በመንግስት ሹመኞች ቁጥጥር ስር የዋለውን መጅሊስ ተቀባይነት የነሳውና ለመሪ ተቋሙ መመለስም እስካሁን እየታገለ ያለው መጅሊሱ የመንግስት ካድሬዎች መጫወቻ በመሆኑ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በመጅሊሱ ስም የሚካሄዱት ሁሉም ተግባራት በመንግስት የሚሾፈሩ መሆናቸውም የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ቆይቷል፡፡ የዛሬውን ዜና ልዩ የሚያደርገው ግን መንግስት ‹‹ሽብርተኝነት›› እና ሌሎች የማስመሰያ ስሞች ሳያስፈልጉት ‹‹እኔ የመረጥኩልህን እምነት አልተከተልክም፤ እኔ በሾምኩልህ ኢማም አልሰገድክም›› ሲል በግልጽ በሰነድ ጭምር ምስክር ጠርቶ ችሎት ፊት ሰዎችን ማቆሙ ነው፡፡ ይህም ይፋ መውጣቱ መንግስት የደረሰበትን የሃይማኖታዊ አፈና ደረጃ ለመላው ዓለምና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት ይበልጥ ይፋ የሚያደርግ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡

አዎን! የመንግስት ሃይማኖታዊ ጭቆና በምንም መልኩ መደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ግን ከሁለት አመታት በላይ ኢ-ፍትሀዊነትን ሲታገል የቆየው ህዝበ ሙስሊም የበለጠ በትግሉ ላይ እንዲጠናከር የሚያደርገው እንጂ ተስፋ የሚያስቆርጠው አይደለም፤ ህዝብ ተስፋ አይቆርጥም! ህዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖት ነጻነቱ እስኪከበርና የዜግነት መብቱን የሚጋፉ አሰራሮች እስኪቀረፉ ድረስ በጽናት መታገሉን ይቀጥላል፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!!!

ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
See More

Sunday, February 23, 2014

★  ሬዲዮ ቢላል Radio Bilal FEB 22 2014 ★  
3ተኛ ልዩ የሙከራ ስርጭት!!
የአማርኛ ስርጭት (Amharic)
--Click http://goo.gl/VWQWb4
--Click http://goo.gl/VWQWb4
የእለተ ቅዳሜ  ሬዲዮ ቢላል መሰናዶ እንዳያመልጥዎ!!!
3ተኛ ልዩ የሙከራ ስርጭት!!
በዛሬው መሰናዶ ፡- ታዋቂው ሸህ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ 
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለህዝበ ሙስሊሙ ያስተላለፉት መልዕክት ፡- 
“የ 39 ዓመቱ ትሩፋት” የሚለን የማስታወሸ ገጾች፡- 
ሸህ እንድሪስ ቂሊንጦ ለመሄድ አስበዋል..ምን አጋጥሞዓቸው ይሆን?:- 
ሰሞነኛ መወያያ  አጀንዳዎችና ዜናዎችን የሚያስቃገኘን ቆይታም አለን…
ቢያመልጦት…ይቆጫሉ!!! 
አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ላልሰሙት ማዳረስን እንዳይረሱ!
ዳውንሎድ በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶ ማስተላለፍን እንዳይረሱ ሊንኩን በመጫን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ።
★★ዳውንሎድ ሼር ማድረጉ የርሶ ድርሻ ነው ሬዲዮ ቢላል ጀዛከላህ ነው ★★
Bilal Communication Facebook Page https://m.facebook.com/BilalComm
★ ሬዲዮ ቢላል Radio Bilal FEB 22 2014 ★ 

--Click http://goo.gl/VWQWb4
--Click http://goo.gl/VWQWb4...
የእለተ ቅዳሜ ሬዲዮ ቢላል መሰናዶ እንዳያመልጥዎ!!!
3ተኛ ልዩ የሙከራ ስርጭት!!
በዛሬው መሰናዶ ፡- ታዋቂው ሸህ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለህዝበ ሙስሊሙ ያስተላለፉት መልዕክት ፡-
“የ 39 ዓመቱ ትሩፋት” የሚለን የማስታወሸ ገጾች፡-
ሸህ እንድሪስ ቂሊንጦ ለመሄድ አስበዋል..ምን አጋጥሞዓቸው ይሆን?:-
ሰሞነኛ መወያያ አጀንዳዎችና ዜናዎችን የሚያስቃገኘን ቆይታም አለን…
ቢያመልጦት…ይቆጫሉ!!!
አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ላልሰሙት ማዳረስን እንዳይረሱ!
ዳውንሎድ በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶ ማስተላለፍን እንዳይረሱ ሊንኩን በመጫን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ።
★★ዳውንሎድ ሼር ማድረጉ የርሶ ድርሻ ነው ሬዲዮ ቢላል ጀዛከላህ ነው ★★
Bilal Communication Facebook Page https://m.facebook.com/BilalComm
See More
ከ15 ሺህ ህዝብ በላይ የተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ በባህር-ዳር [ፎቶ]February 23, 2014

Update: Watch Video

የተለያዩ መፈክር ያነገቡ ሰልፈኞች በባህር ዳር የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ በመገኘት ሰልፉን ሲጠባበቁ ነበር በአሁኑ ሰዓት ከ15 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ሰልፉን ተቀላቅሏል:: የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ሰልፉን በቀዳሚነት እየመሩ ይገኛሉ::
በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ በመቃወም ነው የባህር ዳር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገው።
ድል የህዝብ ነው!! ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!!  ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!  ብአዴን የአማራውን ሕዝብ አፍኖ መግዛት ያቁም!! የኢሀደግ አምባገነን አገዛዝ ሰልችቶናል!! የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ አውሮፕላን በገዛ ረዳቱ ጠለፋ ተደረገበት… ለምን… ?

5265540-3x2-940x627የኢትዮጵያ አውሮፕላን በገዛ ረዳቱ ጠለፋ ተደረገበት… ለምን…  ?
ዛሬ ወደ ሮም ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መጠለፉን ሰማን። ማነው እንዲህ የደፈረን ብለን አቶ ሬደዋንን ብንሰማቸው ጊዜ “አውሮፕላኑ ሱዳን ላይ አርፎ ነበር ምናልባት ጠላፊዎቹ ያኔ ይሆናል የገቡት” ብለው ተናገሩ።  ኋላ ላይ ሲጣራ ግን ጠላፊው የአውሮፕላን አብራሪው ረዳት  መሆኑ ተሰማ፤  ረዳቱ ጠለፋውን የፈፀመው ዋናው አብራሪ በአውሮፕላኑ መፀዳጄ ቤት ጎራ ባለበት ሰዓት ነው።
ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ…
መላ ምት አንድ፤
ዋና አውሮፕላን አብራሪው ፓይለት በሰላም እየበረረ ሳለ መንገድ ላይ የመፀዳዳት አምሮቱ መጣበት እና ረዳቱን፤ “በሰማይ የሰጠውህን በሰማይ እቀበልሃለሁ” በሚል፤ አደራ በሎት መፀዳጃ ቤት ወገቡን ሊፈትሽ ገባ። ይሄን ጊዜ ረዳቱ ሆዬ “ይሄ ሰውዬ ከመፀዳጃ ቤቱ ሲመለስ ሮም አድርሶ ከዛምም ወደ ፍትህ አልባዋ ሀገሬ ከሚመልሰኝ አሁን መሪውን እንደጨበጠኩ የራሴን እድል በራሴ ለምን አልወስንም” አለ እና … መሪውን አለቅም አለ። ሰዊስ ጄኔቭ ላይም ጥገኝነት ትሰጡኝ እንደሆን ስጡኝ ብሎ አሳረፈው።
መላ ምት ሁለት፤
ዋና አብራሪው እና ረዳቱ ቀድሞውኑ ተነጋግረው ነበረም ይሆናል። (ምንም እንኳ ይቺ ዋና አብራሪውን የምታስፎግር መላ ምት ብትሆንም ከጠረጠርን ጠረጠርን ነውና እንናገራለን)
ገና ከኢትዮጵያ ሰማይ ላይም ሳይወጡ፤ ረዳቱ እና ዋናው ኢትዮጵያ መሬት ላይ እያሉ ምሬቶቻችውን ሲያወጉ ነበር አሉ። በተለይ ረዳቱ የደረሰበትን አስተዳደራዊ በደል ሁሉ ዘረዝሮ ለዋናው አብራሪ በነገረው ጊዜ ዋና አብራሪውም በረዳቱ የደረሱ በደሎች በሙሉ በሱም እንደ ደረሱ ነግሮት ስቀሰቅ ብለው ተላቀሱ። ከዛም ረዳቱ አለው፤ “ላንተ እና ለሀገሬ እግዜር መላ እንዲያበጅላችሁ እፀልያለሁ ለእኔ ግን አንድ መላ አብጅቻለሁ” አለው። ቀጠለናም አንተ የምትተባበረኝ አንድ ነገር ብቻ ነው… ሲል ነገረው። “አንተ የሁነልህ እንጂ ችግር የለም ምን ለተባበርህ…” አለው ዋናው አብራሪ… በነገው በረራ የሆነው ቦታ ላይ መፀዳጃ ቤት ገብተህ ትንሽ ቆይታ አድርግ…! አለው አደረገም የሆነው ሁሉም ሆነ።
ከዚህ  ምን እንገነዘባለን፤
አንድ ወዳጃችን በፌስ ቡክ ገፁ “ነገ ከነገ ወዲያ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አውሮፕላን ጠለፈው ጥገኝነት ጠየቁ  የሚል ዜና መስማታችን አይቀርም” ብሎ እንደጠረጠረው በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የደላው ማንም እንደሌለ በቅጡ  እንረዳለን። ከአውሮፕላን ረዳት እስከ ታክሲ ረዳት እና ቤተሰብ ረዳት በሙሉ በፍትህ እጦት “የተማረረበት ሁኔታ ነው ያለው”
በመጨረሻም፤
ያማንማረርባት እና የማንባረርባት ኢትዮጰያ ትመጣ ዘንድ እንፀልያለን።

የጉራጊኛ ዘፋኙ በንግድ ሱቅ ውዝግብ በአጎቱ ተገደለ

የጉራጊኛ ዘፋኙ ፍታ ወልዴ በንግድ ሱቅ ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት የእናቱ ወንድም በሆነው አጎቱ ባለፈው ሰኞ በጥይት ተደብድቦ ተገደለ፡፡ ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን የሟች አስከሬን ወደ ትውልድ ሃገሩ ተወስዶ የቀብር ስነ ስርአቱ ተፈፅሟል፡፡
ሟች እና ገዳይ ከስጋ ዝምድናቸው ባሻገር ከአመታት በፊት በፈጠሩት የልብ ወዳጅነት ነበር መርካቶ በሚገኘው አትክልት ተራ አካባቢ የንግድ ሱቅ የተከራዩት፡፡ ገዳይ የቤቱን ግማሽ አከራይቶ የተቀረውን የአሣ ንግድ ሲያካሂድበት፣ ሟች በበኩሉ ከሙዚቃ ስራው ጎን ለጎን የተለያዩ ተባራሪ ስራዎችን እየሰራ ኑሮውን ይገፋ እንደነበር ምንጮቻችን ይገልፃሉ፡፡
ከጊዜ በኋላ ነው ሟች የሱቁ ባለድርሻነት ጥያቄውን ያነሳው፡፡ ጉዳዩ እስከ ፍርድ ቤት ደርሶም የንግድ ቤቱን ሟች እንዲያስተዳድረው ወደሚል ውሳኔ ይቃረባል፡፡ ይሄኔ ገዳይ “ሁሉም ይቅርና በጋር እንስራ” የሚል ሃሳብ ማቅረቡን የሚናገሩት ምንጮች፤  ሟች ግን በዚህ አልተስማማም ይላሉ “እስከዛሬ በጋራ ፍቃድ እናውጣ ስልህ አሻፈረኝ ብለህ ለኔ ሊወሰን ሲል ነው እንዲህ የምትለው” በማለት ሃሳቡን ሳይቀበለው ቀረ፡፡ ሁለቱን ለማስማማት ጣልቃ የገቡ ሽማግሌዎችም የሱቁ ጉዳይ የመጨረሻ እልባት እስኪያገኝ ገዳይ በኢኮኖሚ እንዳይጎዳ ሟች በወር 4ሺህ ብር እንዲከፍለው አስማሟቸው ይላሉ – ምንጮች፡፡
ከስምምነቱ በኋላ ሟች እና ገዳይ ሰላማዊ ግንኙነት መቀጠላቸውን ያስታወሱት ምንጮች፤ በመሃል ገዳይ “4ሺህ ብሩ አይበቃኝም” የሚል ጥያቄ ማንሳቱን ይናገራሉ፡፡ ባለፈው ሰኞ ገዳይ ሟችን ልጋብዝህ በማለት መርካቶ ሰባተኛ አካባቢ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ ከተገናኙ በኋላ በሽጉጥ ሶስት ጊዜ ተኩሶ እንደገደለው ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ ነዋሪነቱ መርካቶ 7ኛ አካባቢ የነበረው ሟች፤ ባለትዳር እና የልጆች አባት ሲሆን አስከሬኑ ረቡዕ እለት ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ሰባት ቤት ጉራጌ መሸኘቱንና የቀብር ስነ-ስርአቱም እዚያው መፈፀሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ፤ ገዳይን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን እያጣራ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
ሟች ፍታ ወልዴ ቀደም ሲል ከተለያዩ አርቲስቶች ጋር የጉራጊኛ ዘፈን አልበም ያወጣ ሲሆን በቅርቡም የራሱን አልበም እንዳወጣ ታውቋል፡፡

Saturday, February 22, 2014


ባሶንዳ በተባለችዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማ 77 ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል ተባለ
(ቢቢኤን) ከመተማ ቀጥላ በምትገኘዉ ባሶንዳ በምትባለዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማና አካባቢ በኢዮጵያዉን ሽፍቶችና በሱዳን ሽፍቶች መካከል የተነሳዉን ግጭት ተከትሎ አራት ሱዳናዉያን በመሞታቸዉ ሳብያ ለብቀላ የተነሱት ሱዳናዉያን ታጣቂ ሐይላት ኢትዮጵያዉይንን በጅምላ እየገደሉ ነዉ አገር ወገን የድረስልን ሲሉ ወደ ሱዳን በመተማ በኩል የገቡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተጣሩ ነዉ።

አራት ሱዳናዉያን ስለሞቱ በመቶ ኢትዮጵያዊ ነዉ የምንበቀለዉ ያሉት ሱዳናዉያን እስከ አሁን 77 ኢትዮጵያዉይንን መገደላቸዉን በኩራት ይናገራሉ ያሉት ኢትዮጵያዉያን የአብዛኛዎቹ ሟቾች መቃብር የማታወቅ መሆኑንም ይናገራሉ። በየጫካዉ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን አስክሬናቸዉ ለዱር አራዊት መወርወሩን የሚገልጹት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሌላ 42 ኢትዮጵያዉያን የተቀበሩበት መቃበር መኖሩንም ይጠቁማሉ፤ ይህ መቃብር ግን ከሞቱት 77 ሰዎች ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ይኑር አይኑር የሚያዉቁት ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ
በህዳር 24/2006 የሱዳኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊ አህመድ አልቀርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሱዳንና ኢትዮጵያ ያላቸዉን የድንበር ልዩነት አስወግደዉ መስማማታቸዉን ይፋ አድርገዋል። ይህንንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ለስራ ጉብኝት አቅንተዋል። የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኡመር ሐሰን አልበሽር ሁለቱ አገራት በጥበቃ፣በደህንንነት፣ ህገወጥ የሰዉና አደንዛዥ እጽ ዝዉዉርን ለመግታት መስማማታቸዉን ገልጸዋል። በሱዳኗ ባሶንዳ የኢትዮጵያዉያን በጅምላ መገደል ከዚሁ የደህንነት ስጋት ጋር ግንኙነት እንዳለዉ ባይታወቅም ሱዳናን ኢትዮጵያ ግድያዉን ለማስቆም ምንም አይነት ጥረት እንዳላደረጉ ከጥቃቱ የተረፉ ኢትዮጵያዉያን ያስረዳሉ
በየካቲት 11/2006 ህወሃት የተመሰረተበትን 39 አመት ለማክበር የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ልዩ የክብር እንግዳ ሆነዉ መቐሌ ድረስ መምጣታቸዉ ታዉቋል። የሁለቱ አገራት መሪዎች ስለ ቀድሞ ስማእታት ቢናገሩም ወደ ሱዳን በኢኮኖሚ ሳቢያ ተሰደዉ ስለሚሞቱት ኢትዮጵያዉያን ምንም ያሉት ነገር አልነበረም። በባሶንዳ ሱዳን ኢትዮጵያዉያን ነጥሎ የማጥቃቱ ዘመቻ እንደቀጠለ ነዉ! ኢትዮጵያዉያን ወገን ይድረስልን ሲሉም ይጣራሉ።