Sunday, March 2, 2014

የሒጃብ ዋጋ በኛዋ ኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች እና በአሜሪካ ትምህርት ቤት ‪#‎EMUS‬ አጃዒብ ነው

የሒጃብ ዋጋ በኛዋ ኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች እና በአሜሪካ ትምህርት ቤት ‪#‎EMUS‬ አጃዒብ ነው አንብባችሁ አጋሩ
የአሜሪካ ግዛት በሆነው ሚቺጋን የሚገኘው የ‘ብራይቶን’ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙስሊም ያልሆኑ ተማሪዎች በትምህርት ክፍለ ጊዜያቸው ለአንድ ቀን ሙሉ ሒጃብ ለብሰው ዋሉ #EMUS
በብራይቶን /Brighton/ ሃይስኩል የሚማሩ ብዛት ያላቸው የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎች ና መምህራቸው ባለፈው የታህሳስ ወር ላይ ነበር ላንድ ቀን ሙሉ በምርጫቸው ሒጃብን ለብሰው ማ ሻ አላህ በሚያስብል መልኩ አጊጠውበት የዋሉት:: ይህን ውሳኔ እንዲወስዱ ያደረጋቸው በዕለቱ ስለ ሃይማኖት ና ማንነት ርዕሰ ጉዳይ በነበራቸው ክፍለ ትምህርት የሙስሊም ሴቶችን ያለባበስ ስርዓት ለመማር የታቀደ ስለነበር ነው::

በወቅቱም በጽንሰ ሃሳብ /Theory/ ደረጃ ጉዳዩን ከማውራት ይልቅ ተማሪዎቹ ና መምህሯ ራሳቸውን በቦታው በማስቀመጥ እንደ ሙስሊም ሴት ሒጃብ መልበስ የሚኖረውን ስሜት በራሳቸው ላይ በማንጸባረቅ ትምህርቱን ወደራሳቸው ህይዎት ለማዋሃድ የተጠቀሙበት ስልት ነው:: ጉዳዩም ሙስሊም ሴቶች እንደ ሙስሊምነታቸው ሂጃብን በመልበስ ማንነታቸውን /Muslim Identity/ እንዴት እንደሚያንጸባርቁ ለመገንዘብ አጋዥ ነበር:: በተያያዥነት ሒጃብ እንደ የአንድ ማህበረሰብ ግብረ ገባዊ መገለጫነት ሲቀመጥ ለጨዋ ስነ ምግባር ያለውን ሚና በተግባር የሞከሩበትም ነበር::

ከየትኛውም የእድሜ ደረጃ ይልቅ በወጣትነት የሃይስኩል ዕድሜ ላይ የምንለብሰውን ነገር የመወሰን ምርጫችን ራሳችንን እንዴት እንደምናይ /ማንነታችንን በመገንባት ና በማንጸባረቅ/ በእጅጉ ይወስነዋል:: ተማሪዎች በዚህ ሂደት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ሃይማኖት : ባህል ና ማንነትን በመረዳት ሂደት ተግባራዊ የህይዎት ልምድ ና ትምህርት ቀስመውበታል::

በዚህ ምንም ሙስሊም ተማሪ በሌለበት እና አንድ ብዙም ሃይማኖተኛ ያልሆነች ሙስሊም መምህርት ባለችበት ሁኔታ ሂጃብን አድርጎ የመማር ማስተማር ድርጊት መከናወኑ የተወሰኑ አስተያየት ሰጪዎችን ባለባቸው የኢስላም ና ሙስሊሞች ላይ ጥላቻ ሳቢያ ሲያናጫቸው ሰንብቷል:: አንዳንዶቹ ይህን ዜና ባሰራጩ የዜና ማሰራጫ ድህረ ገጾች ላይም ተማሪዎቹ ና መምህሯ ሂጃብ መልበስ 'ለምን ሲባል ሞከሯት : እንዴትስ ተደፈርን' በሚል ዘራፍ ሊሉም ሞክረዋል::
ይህም ድርጊታቸው ከሃገራችን የትምህርት ተቋማት አመራሮች ና ፖሊሲ አውጭ የመንግስት አካላት ጋር አንድ ያደርጋቸዋል:: በሃገራችን የትምህርት ተቋማት እየተማሩ ባሉ እህቶቻችን ሂጃብ መልበስ አይናቸው የደም እንባ ሲያነባ እያስተዋልነው ያለ ጉዳይ ነውና::
ይህ በንዲህ እያለ በሃገራችን ባሉ ሁለተኛ ደረጃ ና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ዩኒቨርስቲ ና ኮሌጆች ያሉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሃይማኖታችን ግዴታ ያደረገብንን የሒጃብ ና ሰላት ድንጋጌዎች በትምህርት ተቋማት መተግበር እርም ሊያደርጉ በየጊዜው ደፋ ቀና እያሉ ነው:: እኛ ግን መቸም አንሰማቸውም : አንቀበላቸውም : መስሚያ ጆሮ የለንም:: የማነታችን ና ህልውናችን አካል በሆኑ በሃይማኖታዊ ግዴታወቻችን ላይ አንደራደርም:: ህገ መንግስታዊ የሰብዓዊ መብታችን ነው:: ከነማንነታችን የዜግነት ሃይማኖት ና ብሄር ሙሉ ስብዕናችን መብታችን ተከብሮ እንማራለን::
በዚህም መንግስት ና በየደረጃው ያሉ ጀሌዎቹ መሰረታዊ የህገ መንግስት መርሆችን በመጻረር የተማሪዎችን የማመን : እንዲሁም በግል ና በቡድን ሃይማኖታቸውን የመተግበር ና የማንጸባረቅ መብታቸውን ተጋፍቷል:: ከመጋፋት አልፎ በፍጹም ሊነጠቅ ና ሊገፈፍ የማይችል የመማር ሰብዓዊ መብታችንን በሃይል ሲገድብ እያየን ነው:: መንግስት ከዚህ መሰል ድርጊቱ መታቀብ ሊኖርበት ይገባል::
ከዚህ ና መሰል የሌሎች ሃገሮች ተሞክሮዎችም ልምድን በበቂ ቀስሞ : አስተሳሰቡን ና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ና ተማሪዎች ያለውን አመለካት በመግራት : የሙስሊሙን መብት ያከበረ : በልማቱም ተሳታፊና ተጠቃሚነቱን ያረጋገጠ ፖሊሲ ና መመሪያ አርቅቆ በማስፈጸም አብሮን ሊሰራ ይገባል::

እኛ ወጣቶች ወደ ጎልማሳነት የእድሜ ገደብ ስንሻገር ባንድ ጠባብ ሂደት ውስጥ እናልፋለን:: ይህም በአቻዎቻችን ባህሪ ና አመለካከት ተገዢ በመሆን በተጽዕኗቸው ስር መውደቅ ወይንም የራሳችንን የጠራ የግል አቋም በማንጸባረቅ ማንነታችንን መገንባት::

ከዚህ አንጻር እኛ እንደሙስሊም ሃይማኖታችን ዲነል ኢስላም ያዘዘንን ማንኛውም ነገር በራሳችን ላይ ከመፈጸም ሊያግደን የሚገባ ተጽዕኖ ሊኖር አይገባም:: ሙስሊምነታችን ኩራታችን : እስልምና ጌጣችን : ሱና ሃብታችን : ሒጃብ ማንነታችን :ሰላት ህልውናችን ነው::

‪#‎የተማሪዎችጉዳይ‬ ‪#‎የትውልድጉዳይነውና‬ ‪#‎የህዝብጉዳይነው‬

አላህ በቂያችን ነው! ድልም ከአላህ እንጅ ከሌላ አይደለም!
አላሁ አክበር!
ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ ግዴታዎን ይወጡ፡፡
**************
ወደዚህ ፔጅ ወዳጅ ዘመዶችዎን በፌስቡክ በመጋበዝ የበኩልዎን ይወጡ : መረጃዎችንም ሼር (SHARE), ላይክ (LIKE) እና ታግ (TAG) በማድረግ እናዳርስ

No comments:

Post a Comment