Monday, March 31, 2014

ፖሊሱ ሚኒባሷን በጥይት መታት፤ አንዲት እህት ወዲያው ሞተች ሁለቱ ቆሰሉ

 

የህዝብን ደህንነት እንዲጠብቁ የሰለጠኑ ፖሊሶች የንፁሀንን ህይወት በማጥፋት ስራ ላይ ተጠምደዋል
news
ትላንትና ማታ ከእምድብር ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ በአካባቢው የጥበቃ ተረኛ በነበረ ፖሊስ በጥይት ከተመታ በኋላ በውስጡ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መሀከል የአንድ ከአረብ ሀገር ተመላሽ እህታችን ህይወት ወዲያው ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ተከስቷል ይላል ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ።
እንደደረሰው መረጃ ከሆነ ፖሊሱ ይህን እርምጃ የወሰደው ሚኒባሱ ኮንትሮባንድ የጫነ መኪና መስሎት እንደሆነ በአካባቢ የነበሩ የአይን እማዬች ቢገልጹም የጥበቃ ፖሊሱ ይህን እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ወደ ላይ ተኩሶ መኪናውን ለማስቆም ወይም ለማስጠንቀቅ ያደረገው ጥረት አለመኖሩን አክለው ይገልፃሉ።
አደጋው የደረሰው በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ልዩ ስሙ ጋሶሬ እየተባለ በሚጠራው መንደር ሲሆን በቅርብ ጊዜ ይህ አካባቢ ከወልቂጤ ከተማ ተካሏል) የእምድብር ከተማ ነዋሪ የሆነችው ሟች ኮከቤ አለማየሁ ባለ ትዳር እና የሁለት ልጆች እናት ስትሆን በቅርብ ጊዜ ከአረብ ሀገር ተመልሳ ኑሮዋን ለማቸነፍ አነስተኛ ሱቅ ለመክፈት ለሱቅ እሚሆን እቃ ለማምጣት ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘች በነበረበት ጊዜ ነው የለፋችለት ትዳሯን እና መስዋዕት የከፈለችላቸውን ልጆቿን ለሚያሳጣት ጥይት በፖሊሱ የተላከባት። አስክሬኑ ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወስዷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስት በታጠቁ ፖሊሶች ህይወታቸው እየተነጠቁ ያሉ ምስኪን ዜጎች ቁጥር በሀገራችን እየጨመረ ይገኛል።
ለሟች ቤተሰቦች ሀዘኑ መራራ ቢሆንም መጽናናትን ለቆሰሉ ቁስላቹ የውሻ ቁስል ይሁንላቹ የሚሉት የዚህ ዘገባ አጠናቃሪዎች “የንፁሀንን ደም ለማጥፋት የሰለጠኑ የሚመስሉትን ፖሊሶችን እያሰለጠኑ ለሚያወጡ ማሰልጠኛዎች እባካችሁ ምልመላና የስልጠና አሰጣጣችሁን በመቀየር ፖሊስ የንፁሀን ጠባቂ እንጂ ስጋት መሆናቸውን አስቁሙልን” ሲሉ ጥሪያቸውን ያቀርባሉ”"

Saturday, March 29, 2014

ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው


ህጉ ጣጣ እንዳያመጣ የሰጉ ኢህአዴግን እየመከሩ ነው
http://www.goolgule.com/eprdf-to-enforce-strict-religious-laws/

ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ... ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው።

ጎልጉል ከዲፕሎማት ምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ኢህአዴግ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅበትንና ከሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውጭ መሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግንና የተቃውሞ ድምጽ ማሰማትን የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል።

የዜናው ምንጮች ዝርዝር ህጉን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ እንደሚቆጠቡ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የሚደነገገውን አዲስ ህግ ጥሰዋል በሚል የሚከሰሱ ምዕመኖች እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የሚያዝ አንቀጽ አለበት። አዲሱ ህግ ከሽብርተኞች ህግ ጋር የሚጣቀስ እንደሆነም የጠቆሙት ክፍሎች ኢህአዴግ “ከእምነት ነጻነት” ጥያቄ ጋር በተያያዘና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ውስጥ ውስጡን እየነደደ ያለው ችግር ስላስጨነቀው ይህንን ህግ ለማውጣት መገደዱን አስረድተዋል። በሌላ በኩልም እስካሁን መፍትሔ ያላገኘው የሙስሊሞች ጥያቄ ከዚያም ጋር ተከትሎ የተከሰተው ደም መፋሰስ ወደፊት ሊያመጣ በሚችለው ጉዳይ ላይ ኢህአዴግን በብርቱ አሳስቦታል፡፡

ኢህአዴግ ከቀን ወደ ቀን ቀውስ እየተደራረበት እንደሆነ የተረዳችው አሜሪካ በከፍተኛ ባለስልጣኖቿ አማካይነት ኢህአዴግን እየመከረች እንደሆነ ከዲፕሎማቶች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ከፖለቲካው ቀውስና በቀጠናው ካለው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አሜሪካ በተደጋጋሚ የህወሃትን ሰዎች በተናጠል እያነጋገረች እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ዲፕሎማቶቹ እንደሚሉት አሜሪካ መለስ “ከተሰዉ” በኋላ አገሪቱን ማን እየመራት እንደሆነ በቅጡ ለመረዳት በሚያስቸግር ሁኔታ የስልጣን መዛነፍና ደረጃን የጠበቀ የስልጣን ተዋረድ አለመኖሩም አሳስቧታል። ኢህአዴግ ለህልውናዬ ያሰጋኛል በሚል መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች /መያዶች/ ላይ ያወጣውን አፋኝ ህግም ጠቅሰዋል። ዲፕሎማቶቹ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ወቅቱ አሁን እንዳልሆነ አመልክተዋል።
*************************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
See More
Like · ·

ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው

ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው።ጎልጉል ከዲፕሎማት ምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ኢህአዴግ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅበትንና ከሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውጭ መሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግንና የተቃውሞ ድምጽ ማሰማትን የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል።
Freedom of Expression For All Ethiopian Peoples , NOW ! ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፣ አሁኑኑ ! Free all Ethiopian Jornalist and Political Prisoners, Stop...

Tuesday, March 25, 2014

የሙሥሊም መሪዎች የክስ ሂደት

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ችሎት በዛሬው ውሎው የሙሥሊም መሪዎችን የክስ ሂደት ተመለከተ። ችሎቱ በነአቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ ዓቃቤ ሕግ በአሸባሪነት ክስ የመሠረተባቸውን ተከሳሾች ጉዳይ ከተመለከተ በኋላ
Waage der Göttin Justitia
የመከላከያ ምስክሮችን ለማዳመጥም ለፊታችን ሀሙስ መጋቢት 18 ቀን ፣ 2006 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዞዋል። ችሎቱ ተከሳሾች በማረሚያ ቤት ውስጥ ደረሰብን ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰትንም በማዳመጥ ፣ ተከሳሾች አቤቱታቸውን በጠበቆቻቸው በኩል እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
አርያም አብርሀ
ነጋሽ መሀመድ

የግብጽ ፍርድቤት 530 በሚሆኑ የሙስሊም ወንድማማች አባላት ላይ ሞት ፈረደ ተከሳሾቹ ለአንድ ፖሊስ ኃላፊ መሞት ተጠያቂዎች ናቸው


egypt 5
* ውሳኔው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን አስደንግጧል
በሕዝብ ከተመረጡ በኋላ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው የተወገዱትን የቀድሞ የግብጽ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲን በመደገፍ በፖሊስ ጣቢያ ላይ አደጋ አድርሰው የነበሩ 529 ተጠርጣሪዎች ትላንት ሰኞ ዕለት የሞት ቅጣት ተበየነባቸው፡፡ የብይኑ ፍጥነትና የተፈረደባቸው ተከሳሾች ብዛት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን አስደንግጧል፡፡ አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ከሆነ ውሳኔው ለይግባኝ የሚቀርብ ሲሆን በሙስሊም ወንድማማች ላይ ሆን ተብሎ የተነጣጠረ ጥቃት እንደሆነ ዘግቧል፡፡
egypt 3በዓለማችን በቅርብ ጊዜያት ከተካሄዱ የሞት ፍርድ ብያኔዎች በብዛትም ሆነ በፍጥነት ለየት ያለ እንደሆነ የተጠቀሰለት ይህ የፍርድ ሂደት በግብጽ የሕግ የበላይነት እየከሰመ የሄደ መሆኑን የሚያመላክት ነው ሲሉ በርካታ የሕግ ምሁራን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ተከሳሾቹ በሙሉ የሙስሊም ወንድማማች አባላትና የቀድሞው ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ ደጋፊ መሆናቸው ብያኔው እውነተኛ የፍርድ ሂደት የተከተለ ሳይሆን ወደፊት ሊነሳ ለሚችል ተቃውሞ ማስተማሪያ እንዲሆን ታቅዶ የተከናወነ ነው ሲል የፍትሕ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ አሶሺየትድ ፕሬስ በተጨማሪ ዘግቧል፡፡
ተከሳሾቹ የቀረበባቸው ክስ ባለፈው ነሐሴ ወር ሚኒያ በተባለች የግብጽ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት በተከናወነ የነፍስ ግድያ፣ የግድያ ሙከራ፣ መንግሥትን ለመገልበጥ ሕገወጥ ቡድንን መቀላቀል እና የመንግሥትን የጦር መሣሪያ መስረቅ በሚሉ ወንጀሎች ናቸው፡፡ በወቅቱ በፖሊስ ጣቢያው ላይ በደረሰ ጥቃት የሚኒያ ከተማ ምክትል የፖሊስ ኃላፊ ሞሐመድ አል-አታር መገደላቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጥቃት በኋላ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዘው ወታደራዊው አገዛዝ በሙስሊም ወንድማማች ደጋፊና አባላት ላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነና አሰቃቂ ጥቃት በማድረስ በዚያን ወቅት ብቻ ከ600 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል፡፡
ከ545 ተከሳሾች ውስጥ 528ቱ ጥፋተኞች ሆነው በመገኘታቸው የሞት ፍርድ እንደተበየነባቸው የመንግሥት ሚዲያ ሲያስታውቅ አንዳንድ ባለሥልጣናት ቁጥሩ 529 እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 150 በሌሉበት ፍርዱ የተበየነባቸው ሲሆን የተቀሩት ግን በነጻ ተለቅቀዋል፡፡ በግድያው የተሳተፉት ብቻ ፍርድ ሊበየንባቸው ይገባል በማለት የሚከራከሩ ወገኖች እንደሚሉት በማስረጃነት የቀረቡት 20 የሚሆኑ የቪዲዮ ምስሎች እንደሚያሳዩት የተወሰኑ ሰዎች የፖሊስ አዛዡን በብረት በትር ሲደበድቡ እና አንድ ሐኪም ደግሞ በእሣት ማጥፊያ የኦክስጂን ሲሊንደር (ካንስተር) የፖሊሱ ጭንቅላት ሲፈረክስ ታይቷል ይላሉ፡፡
መሐመድ ሙርሲ
መሐመድ ሙርሲ
ሁለት ቀናት ብቻ በፈጀው በዚህ የፍርድ አሠጣጥ ሥርዓት ላይ የተከሳሽ ጠበቆች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የማስረጃ ሰነዶችን ለመመልከትም ሆነ በቂ ጊዜ አግኝተው የደንበኞቻቸውን ጉዳይ ለፍርድቤቱ ለማስረዳት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ከፍተኛ ባለስልጣን ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደገለጹት ከዚህ ዓይነቱ የሞት ብያኔ በኋላ ማንም በተመሳሳይ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደማይሳተፍ ጠቁመዋል፡፡ የፍርዱን አካሄድ ሲገልጹም “ሁኔታው እጅግ ለየት ያለ ነው፤ እያንዳንዱን ተከሳሽ እየጠራን ክሱን እንዲከራከር፣ ጠበቃ እንዲያቆም፣ ወዘተ ለማድረግ በቂ ጊዜ የለንም” ብለዋል፡፡ በፍርዱ ሂደት ላይ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸው በጠየቁ ጠበቆች ላይ ችሎቱ የመሩት ዳኛ ሰዒድ ዩሱፍ ጠበቆቹን በቁጣ መዝለፋቸው አብሮ ተዘግቧል፡፡
የሞት ፍርዱ በግብጽ ሙፍቲ (የአገሪቱ ከፍተኛ እስላማዊ ባለሥልጣን) መጽደቅ ያለበት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የተከሳሽ ጠበቆች ይግባኝ በማለት ፍርዱን ለማስቀየር እየሠሩ መሆናቸው ተገልጾዋል፡፡
ሞሐመድ ባዴይ
ሞሐመድ ባዴይ
ሌሎች ወደ 700 የሚጠጉ የሙስሊም ወንድማማች ተከሳሾች ዛሬ ማክሰኞ ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል የወንድማማቹ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ሞሐመድ ባዴይ እና ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች ይገኙበታል፡፡ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሙርሲም በቅርቡ ለፍርድ የሚቀርቡ ሲሆን ዛሬ የሚቀርቡትን ጨምሮ ሙርሲም ሞት ሊፈረድባቸው ይችላል የሚል አስተያየት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ዓለምአቀፍ ተጽዕኖን በመፍራት ሙርሲ ላይ ሞት የመፈረዱ ጉዳይ አጠራጣሪ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አመልክተዋል፡፡
የሰኞ ዕለቱን ብያኔ ተቃውሞ የቀረበበበትን ያህል የፍርዱን ትክክለኛነት የደገፉ ግብጻውያንም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አሚን ፍቱሕ የተባሉ የካይሮ ነዋሪ ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደተናገሩት “ቁርዓን እንደሚለው ገዳዮች ሞት ይገባቸዋል፤ እነዚህ ሰዎች ግድያ ስለፈጸሙ በአጸፋው መገደል ይገባቸዋል” ብለዋል፡፡
ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሰኞው ዕለት ፈጣን የሁለት ቀን ብያኔና በቀጣይ የሚደረጉት የፍርድ ሂደቶች እጅግ ያሳሰቧቸው መሆኑ ገልጸዋል፡፡ አምነስቲ ብያኔውን “በቅርብ ዓመታት በዓለማችን ከተካሄዱ የሞት ብያኔዎች በዓይነቱ ብቸኛው” በማለት ሲገልጸው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ደግሞ “ኅሊናን የሚያስደነግጥና የፍትሕ ውርጃ የታየበት” ነው ብሎታል፡፡ (ፎቶ: AP እና BBC)

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Sunday, March 23, 2014

የስፖርት ጋዜጠኞች የተያያዙት ማዝናናት ወይስ ማዘናጋት?

 በግሬስ አባተ
አሁን ባለንበት ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሁሉም ነገር በሚባል ሁኔታ ጮክ ተብለው የሚወሩት ሁለቱ ነገሮች ናቸው፡፡ አንደኛው የአውሮፓ እግር ኳስ ሲሆን ሁለተኛው ፆታዊ ግንኙነትን Imageየተመለከቱ ርዕሶች ናቸው፡፡  በዚህ ፅሁፍ ለመዳሰስ  የፈለኩት በአውሮፓ እግር ኳስ  ዙሪያ የመገናኛ ብዙሃንን ያልተገደበ አስተዋዋቂነት ወይም ቲፎዞነት ወይም የማራገብ  ሁኔታ መመልከት፤ እንዲሁም የዚህ ማራገብ አስፈላጊነቱ ለምን እንደሆነ መግለፅ  ይሆናል፡፡
ለመነሻ ያህል በአዲስ አበባ ካሉት የራዲዮ ፕሮግራሞች እንኳን ብንጀምር ምን ያህል ሰአት ለአውሮፓ እግር ኳስ እንደሚሰጡ መታዘብ ይቻላል፡፡ ከሌሎች የራዲዮ ፕሮግራሞች አንፃር አብዛኛውን የአየር ሰአት ተሰጥቶት የሚለፈፈው የእስፖርት ፕሮግራም ነው፡፡  በአዲስ አበባ ካሉት ኤፍ ኤም ራዲዮኖች፤ በእንግሊዝኛ ከሚተላለፈው አፍሮ ኤፍ ኤም  በተስተቀር አብዛኛው ለእግር ኳስ የሚሰጡት የአየር ሰአት ከፍ ያለ ነው፡፡  እንዲሁ ለእግር ኳስ አልኩ እንጂ ይህም ለሃገር ውስጥ ከሚሰጠው የአየር ሰአት ጋር ሲነፃፀር ሰማይና መሬት መሆኑን ዘወትር የምንታዘበው ነው፡፡ ያንበሳው ድርሻ  ለማንችስተርና ለአርሰናል፤ለባርሳና ማድሪድ ወ.ዘ.ተ ይሰጣል፡፡ እዚህ ላይ የአገር ውስጡን ስፖርት እንዲሁ ለቅንነት ያህል ገለፅኩት እንጂ ከማንችስተር እና አርሰናል አንፃር  የአየር ሰአት ያገኛል ለማለት እንኳ አያስደፍርም፡፡
ለምሳሌ ያህል የራዲዮኖቹን አነሳው እንጂ በጋዜጣ የሚታተሙትን እድሜ ጠገቦቹን ኢትዮ ስፖርት፣ ወርልድ ስፖርት፣ዘ-ገነርስ… እማ  95% የሚሆነው የጋዜጣቸው ሽፋን ለአውሮፓ እግር ኳስ እንደሚሰጡ ግልፅ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማለትም በህትመትና በራዲዮ ካሉት በተጨማሪ  ብቸኛው ኢቲቪ(ለነገሩ አሁን ኦሮሚያ ቲቪም የአውሮፓን እግር ኳስን በማስተላለፍ ከኢቲቪ ጋር እኩል እየተጋ ይገኛል፡፡) በነፃ በማስተላለፍ ጠመቃውን እያሳለጡት ይገኛሉ፡፡ አንድ አይነት አካሄድ የሚስተዋልበት ይህ የአውሮፓ እግር ኳስ የጠመቃ አካሄድ ጥርጣሬን ካጫረብኝ ሰንበትበት ብሏል፡፡  እንዳልኩት ሱፐር እስፖርት በክፍያ ኢቲቪና ኦሮሚያ ቲቪ በነፃ በድምፅ እና ምስል የሚያስተላልፉት ሲሆን በራዲዮን በኩል እነ መሰለ መንግስቱ ከሱፐር ስፖርቶቹ ጋዜጠኞች በላይ ሰፊ የአየር ሰአት ወስደው በቀጥታ ያስተላልፋሉ፡፡ ሸገር ኤፍ ኤም ላይም እንዲሁ በየሳምንቱ የሚተላለፍ ፕሮግራም እንዳለ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የየጨዋታዎቹን ውጤት ተከትሎ ትንታኔ የሚሰጡ ጋዜጠኖች ቁጥራቸው የትየሌሌ ነው፡፡ ለዚህ ይመስላል የአውራምባ ታይምሱ አቤል አለማየሁ በአንድ መፅሃፉ ‹‹አንተ ብቻ የስፖርት ጋዜጠና ሁን›› ሲል የጊዜውን ሁኔታ የገለፀው፡፡
በየቀኑ የሚሰጡትን የእግር ኳስ የትንታኔ ሰአቶች እንኳን ትተን በሳምንት የሚሰጠውን የቀጥታ ስርጭት ብንመለከት ጉዳዩ ምን ያህል እየተሰራበት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ለምሳሌ ‹‹እግር ኳስን በራዲዮ ተመልከቱ›› የሚለውን የመሰለን ፕሮግራም ለአብነት ብንወስድ በየሳምንቱ ለአንድ ጨዋታ  በትንሹ 90 ደቂቃ የቀጥታ ጨዋታው + ከጨዋታው በፊት 30 ደቂቃ + 30 ከጨዋታው በሁዋላ ያለውን ብንወስድ በድምሩ በሳምንት 2:30 ይወስዳል፡፡ ይህ በወር ሲመታ፣ በአመት ሲመታ ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል አስቡት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ   ከውጤትና ከጨዋታ በፊትና በኋላ ያሉትን ትንታኔዎች የወሰድን እንደሆነ ከአፍሮ ኤፍ ኤም ውጪ በቀን እያንዳንዱ ራዲዮን በትንሹ 2:00 የአየር ሰአት ለአውሮፓ እግር ኳስ ይሰጣል፡፡ ይህን በሳምንት እንዲሁም በወር ሲመታ አስቡት ምን ያህል እንደሆነ!
የእኔ መከራከሪያ ለምን ስፖርት ተወራ አይደለም፡፡  ጉዳዬ ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ላይ መነሳትም አይደለም፡፡ እርግጥ ነው መናገር መብታቸው ነው፡፡ ስለ ዋይኒ ሩኒ፣ሜሲ፣ሮናልዶ  እድሜ እና ክብደት እንዲሁም ቁመት መናገር ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ነው ከተባለ መቼስ ምን ይደረጋል፡፡ ጥያቄዬ ስለምን ይህን ያህል የአየር ሰአት ተሰጥቶት ሊወራ ቻለ ነው? ይህንን የሚያግዝ በተጨባጭ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን አለ ነው? መቼም አድማጭም ተመልካችም ያለው የአውሮፓ እግር ኳስን ነው፤ የሚል ቀልድ አዘል አስተያየት  አይቀርብም አይባልም፡፡ ይህ ቁጥር ነጋ ጠባ እያሻቀበ እንዲሄድና ወጣቱ ስለ ራሱ የወደፊት ሁኔታ ከመጨነቅ ይልቅ ስለ ማንችስተርና አርሰናል እንዲጨነቅ ነጋ ጠባ የሚለፈለፍለት ስለምን ይሆን? መቼም ከዚህ ጀርባ አንድ ድብቅ ሴራ እንዳለ ግልፅ ነው፡፡
ለዚህም ማጠናከሪያ የሚሆነን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአለም ወንጫ ማጣሪያ ላይ የተከሰተው  ድርጊት  ነው፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ቡድን ሁለት ቢጫ ካርድ ያየ ተጫዋች አላግባብ አሰልፏል ተብሎ 3 ነጥብ እንደተቀነሰበት ሰምተናል፡፡ እዚህ ላይ  መነሳት ያለበት የስፖርት ጋዜጠኞች ድርሻ ነው፡፡ የኛ የስፖርት ጋዜጠኞች ምን ይሰራሉ? የነ ሩኒን ፣ የነቫምፐርሲን፣ የነሮናልዶን ወ.ዘ.ተ ከእግር ጫማቸው እስከ እራስ ፀጉራቸው ሲለፈልፉልን ስለምን ስለአገራቸው እግር ኳስ ቢያንስ በ90 ደቂቃ ውስጥ የተመዘዘውን ቢጫ ካርድ መዝግበው  መያዝ  አቃታቸው? የአርሰናሉ ኮሶሎኒ በሁለት ቢጫ ካርድ ምክንያት በሚቀጥለው ጨዋታ አይሰለፍም፣ ሜሲ እዚህ አገር ተወልዶ እንትን በምትባል መንደር አድጎ ቁመቱ ይህን ያህል ክብደቱ ይህን ያህል የሚሉን የስፖርት ጋዜጠኞች ስለምን የኛን ቡድን የ 90 ደቂቃ ቢጫ እንኳ መቁጠር አቃጣቸው ብለን ስንጠይቅ ሴራው ፍንትው ብሎ ይታየናል፡፡ በማስታወቂያ በኩል ያለውን ብንመከት ድርጅቶች ስፖንሰር የሚያደርጉት የእስፖርት ፕሮግራሞችን 90% ያለፈ መሆኑን ሌሎች ፕሮግራሞች ባንፃሩ የማስታወቂያ ድርቅ ሲመታቸው እንመለለከታለን፡፡ ምነው ይህን ያህል እዚህ አገር ሳናውቀው ኳስ ተዘርቶ ኳስ መታጨድ ተጀመረ እንዴ?
ምንአልባት በደምብ አልገለፅኩት ይሆናል አንጂ አሁን ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ አዘቅት ውስጥ የሚከተን ይሆናል፡፡ አንድ ታዳጊ አገር ያውም ከድህነትና ከችጋር ያልተላቀቀች አገር ውስጥ የተማሩና ገና የመጀመሪያ ደረጃ ትምርታቸውን ያልጨረሱ አፍላ ወጣቶች ሳይቀሩ በአውሮፓ እግር ኳስ ተጠምደው ነጋ ጠባ የሚያሳስባቸው የክለቦቹ መሸነፍና ማሸነፍ ሲሆን ወዴት እየሄድን እንደሆነ እና ሴራው ግቡን እየመታ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በየመስሪያ ቤቱ ስለ አውሮፓ እግር ኳስ  ሲከራከሩ ከፍ ሲልም  ሲደባደቡ መመልከት ብዙም የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ተማሪዎችም በእረፍት ግዜያቸው ሰብሰብ ብለው ሲያወሩ የሚሰሙት   ስለ እግር ኳስ ከሆነ አመታት ተቆጠሩ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ሳይቀሩ የመጀመሪያው ወሬያቸው ስለተሰጣቸው የቤት ስራ ሳይሆን ስለ ማታው ጨዋታ ከሆነ ቆየ፡፡ ገና 10 እና 11 አመት ያልሆናቸው ልጆች ስለምን  ስለ አርሰናል እና ማንችስተር ነጥብ መጣል እንዲሁም ስለ ተጫዋቾች ጉዳት እንዲጨነቁ ተፈረደባቸው?
 ገና ከወዲሁ ትውልዱን በአንድ አይነት አካሄድ የመቅረፅ ሴራ… ከፍ ያለውንም እንዲዝናና ሳይሆን መሬት ላይ ያለውን  እውነት እንዳያይ ማዘናጋት የስፖርት ጋዜጠኖች ድርሻ ከሆነ ቆየ፡፡  ጋዜጠኞቹም ገንዘብ እስካገኙ ድረስ  የትውልዱ እጣ ፋንታ ግድ የሚሰጣቸው እንዳልሆነ አሳይተውናል እያሳዩንም ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ እነሆ ማን ነው ይችን አገር የሚረከባት? መቼም 4-4-2 አሰላለፍ  በስነ-ምግባርና በእውቀት የታነፀ ትውልድ ለመቅረፅ ቀርቶ ቤተሰብን ለመምራት እንኳ አያገለግልምና የትውልዱ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ምን ብናረግ ትውልዱን ከዚህ አይነት አፍዝዝ አደንዝዝ ሴራ ማውጣት እንችላለን? የሚለው የሁሉም የአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ  ድርሻ በመሆኑ፤ ለዚህ ሴራ መክሸፍ የበኩላችንን በማድረግ ትውልዱን ልናድነው ይገባል፡፡

አንበሳ አውቶብስ ተገልብጦ ሰዎች ሞቱ

ዛሬ ማለዳ 12:55 ላይ ከካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ የነበረ የከተማ አውቶብስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ድልድይ ውስጥ ገብቶ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።
አደጋው የደረሰው ከካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው 36 ቁጥር የከተማ አውቶብስ ፥ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው ረዥም ድልድይ ውስጥ በመግባቱ ነው።

በአደጋው እስካሁን አንድ እግረኛን ጨምሮ አራት ወንድ እና አራት ሴት ተሳፋሪዎች ህይዎታቸው ያለፈ ሲሆን 46 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአውቶብሱ አሽከርካሪና ትኬት ቆራጭ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህይወት መትረፋቸው ታውቋል።
ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በጥቁር አንበሳና ጳውሎስ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ሲሆን አውቶብሱን ከገባበት ገደል ለማውጣትም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው።

Yigermal Poem for Berahane Damte (Aba Mela) by Henok Yeshitla

በኢትዮጵያ ትልቁን የወርቅ ክምችት ተገኘ




በኢትዮጵያ ትልቁን የወርቅ ክምችት ተገኘ
* በኢትዮጵያ የወርቅ ፍለጋ ታሪክ ከተገኙ የወርቅ ክምችቶች በሙሉ ይበልጣል ተብሏል፡
አስኮም ማይንኒግ የተባለው የግብፅ ኩባንያ በኢትዮጵያ ታሪክ እስከዛሬ ከተገኘው የላቀ የወርቅ ክምችት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አገኘ፡፡
የተገኘው የፅንስ ወርቅ ክምችት በኢትዮጵያ የወርቅ ፍለጋ ታሪክ ከተገኙ የወርቅ ክምችቶች በሙሉ ይበልጣል ተብሏል፡፡
በቅርቡ ከተደረሰባቸው የወርቅ ክምችቶች መካከል በቱሉ ካፒ ወለጋ ኒዮታ ሚኒራልስ የተሰኘ የእንግሊዝ ኩባንያ፣ በመተከል ሳካሮ በሚድሮክ ጐልድ በኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች በናሽናል ማይኒንግ በአፋርና በትግራይ ክልሎች ስትራቴክስ በተባለው የእንግሊዙ ኩባንያ፣ በትግራይ ክልል በኢዛና ማይንኒግ የተገኙት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የግብፅ ኩባንያ አስኮም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያገኘው የወርቅ ክምችት በእነዚህ ኩባንያዎች ከተገኙት ክምችቶች ሁሉ እንደሚበልጥ ተገልጿል፡፡
የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ቶሎሳ ሻጊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አስኮም ያገኘው የወርቅ ክምችት እስከዛሬ ከተገኙ ክምችቶች ሁሉ የላቀ ነው፡፡ የኩባንያው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ለማዕድን ሚኒስቴር ኃላፊዎች ስላገኙት ግኝት ከሁለት ሳምንት በፊት ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ኩባንያው ባካሄደው የወርቅ ፍለጋ ሥራና ባገኘው ውጤት የሚኒስቴሩ ኃላፊዎች መደሰታቸውን አቶ ቶሎሳ ገልጸዋል፡፡ ‹‹እስከዛሬ ስናወራ የነበረው ስለ 30 እና 40 ቶን የወርቅ ግኝት ነበር፡፡ አስኮም ያገኘው ከዚያ በእጅጉ የሚበልጥ ነው፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ የግብፁ ያገኘው የወርቅ ክምችት መጠን በትክክል ምን ያህል እንደሆነ በአኃዝ ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ የአስኮም ኃላፊዎች ከሁለት ሳምንት በኋላ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አስኮም ማይኒንግ በቀጣይነት የአዋጭነት ጥናት የሚያካሂድ መሆኑን፣ የአዋጭነት ጥናቱን ከሠራ በኋላ ሚኒስቴሩ ከፍተኛ ደረጃ የወርቅ ማምረት ፈቃድ እንደሚሰጠው አቶ ቶሎሳ ተናግረዋል፡፡ ኩባንያው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ማምረት እንደሚጀምር ታውቋል፡፡
በሚድሮክ ኢትዮጵያ ሥር ከሚተዳደሩት በርካታ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ናሽናል ማይኒንግ ኩባንያ በኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ባገኛቸው የወርቅ ክምችቶች ያካሄደውን የአዋጭነት ጥናት ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በቅርቡ እንደሚያቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኩባንያውና ሚኒስቴሩ የጥናቱን ውጤቶች በቅርቡ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ኒዮታ ሚኒራልስ በቱሉ ካፒ ባገኘው የወርቅ ክምችት ላይ የአዋጭነት ጥናት አካሂዷል፡፡ ጥናቱ ከተሠራ በኋላ የወርቅ ዋጋ በማሽቆልቆሉ እንደገና ጥናቱን ለመከለስ ተገዷል፡፡ በዚህም ምክንያት ኩባንያው በአሁኑ ወቅት የተሻሻለ ጥናቱን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አቶ ቶሎሳ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከማዕድናት ኤክስፖርት በዓመት ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የምታገኝ ሲሆን፣ 90 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ምንዛሪ የሚያመጣው ወርቅ ነው፡፡ ወርቅ በአሁኑ ወቅት ከቡና ቀጥሎ ትልቁ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ ምርት ሆኗል፡፡ በየጊዜው ተጨማሪ የወርቅ ክምችቶች መገኘታቸውን የጠቆሙት ጂኦሎጂስቶች፣ ወርቅ የኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

Saturday, March 22, 2014

ከአንድ ሳምንት በኋላ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ተወካዮች ወደ ኢትዮጵያ ያመራሉ

ከአንድ ሳምንት በኋላ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ተወካዮች ወደ ኢትዮጵያ ያመራሉ።‪#‎Ethiopia‬
የአሜሪካ መንግስት በኢትዪጲያ ሙስሊሞች ትግል ዙርያ ከኢትዪጲያውኑ ጋር ተወያየ።
ቢ ቢ ኤን
የኢትዪጲያ ሙስሊሞች የሚያካሄዱትን ሰላማዊ ትግል አስመልክቶ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስቴት ዲፓርተመንት ከፈርስት ሂጅራ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አደረገ፡፡
ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያደረገውን የሁለት አመት ሰላማዊ የትግል ጉዞና የታሰሩትን የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ዙርያ ሰፋ ያለ ውይይት መካሄዱ ታዉቁዋል፡፡ በመጪው አፕሪል 1 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ተወካዮች ወደ ኢትዪጲያ ያመራሉ፡፡ የህዝበ ሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችም ለማግኘት ሙከራ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ ሳዲቅ አህመድ ስብሰባውን አስመልክቶ ዝርዝር ዘገባ አሰናድትዋል::
እርስዎ ለማንበብ ይጠብቁ ። ለበለጠ መረጃ BBN ቢቢኤን የናንተው ድምፅ ዘወትር ይከታተሉ።

Tuesday, March 18, 2014

በናታችሁ አትጨክኑ!!


የበሽታ አይነት ተፈራረቀብኝ ሁሉን ችዬው ኖርኩኝ የአሁኑ በሽታን ግን መቋቋም አቃተኝ በውስጤ ያሉት ቫይረሶች ጎዱኝ በሽታዬ ሱኳር ይሆን እንዴ ቆራረጡኝ እኮ ልጆቼ ለማንም ደርሽ ናቸውሁ ምነው ለኔ መሆን አቃታቸው ሁሉም ጥሎኝ ኮበ...ለለ ከኔ የተሻለ እንጀራ እናት አገኘ የኔን በሽታ ከሩቅ ሆነው ሊያድኑ ይፈልጋሉ እኔ ታምሜ አዳኝ አጥቼ በውስጤ ያሉት ሲፈጁኝ የሚያስጥለኝ ጠፋ ወይ ዘመን እናቱን ለጠላቱ ትቶ ከንጀራናቱ የሚኖር ትውልድ ወልጄ ከንቱ ትንሽ አሉኝ የምላቸውን መዳኒቶች ቫይረሱ ተይዘዋል ብርቅዬ የሆኑ ቫይታሚኖቼን አስሮ ጎዳኝ አሁንስ ተጎዳው አድኑኝ ምንም ድሃ ብሆን እናታችሁ ነኝ ከነዚህ የሱኳር ደዌዎች ቆራርጠው ሳይጨርሱኝ ድረሱልኝ በሽታዬ ታውቋል የቫይረሱ ስም ውያኔ tplf ነው መዳኒቱ አለ በጃችሁ አትሰስቱ በናታችሁ አትጨክኑ!! 

ምንም የረባ መከራክሪያ ያላቀረበው ፖሊስ መናገር አቅቶት ሲንተባተብ ነው የዋለው

ምንም የረባ መከራክሪያ ያላቀረበው ፖሊስ መናገር አቅቶት ሲንተባተብ ነው የዋለው በተጨማሪ ሌሎች መያዝ የልቻልናቸው 20 እሩጫውላይ የነበሩ ሴቶችስላሉ በማለት የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል ሲጀምር ችሎቱ የታየው በጽ/ቤት ነው የነበረው የሰዉ ብዛት ያስጨነቀው መንግስት ሰዉ በችሎት እንዳይታደም ክርክሩን እንዳይሰማ በጣም ጠባብ በሆነችው ቢሮ ከአቅሙዋ በላይ የሆኑ ተከሳሾችን ለማሰተናገድ ተገዳለች ውሳኔ መስጠት የማይችለው ዳኛ ለነገ መጋቢት 10/2006 በመደበኛ ይታይ በሚል ተልካሻ ምክንያት ቀጥሮአቸዋል የጣይቱ ልጆች ግን በጣም በሚያሰድሰት ሞራልና የትግለ ሰሜት ላይ ሆነው ለማየት ችለናል፡፡
BlueParty Ethiopia's photo.
መንግሰት ሰለ ጣይቱ ልጆች ጨንቆት ዋለ
****************************
ምንም የረባ መከራክሪያ ያላቀረበው ፖሊስ መናገር አቅቶት ሲንተባተብ ነው የዋለው በተጨማሪ ሌሎች መያዝ የልቻልናቸው 20 እሩጫውላይ የነበሩ ሴቶችስላሉ በማለት የ14... ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል ሲጀምር ችሎቱ የታየው በጽ/ቤት ነው የነበረው የሰዉ ብዛት ያስጨነቀው መንግስት ሰዉ በችሎት እንዳይታደም ክርክሩን እንዳይሰማ በጣም ጠባብ በሆነችው ቢሮ ከአቅሙዋ በላይ የሆኑ ተከሳሾችን ለማሰተናገድ ተገዳለች ውሳኔ መስጠት የማይችለው ዳኛ ለነገ መጋቢት 10/2006 በመደበኛ ይታይ በሚል ተልካሻ ምክንያት ቀጥሮአቸዋል የጣይቱ ልጆች ግን በጣም በሚያሰድሰት ሞራልና የትግለ ሰሜት ላይ ሆነው ለማየት ችለናል፡፡
ችሎቱንም ለመከታተል የተለያዩ ኢንባሲ ተወካዮች ፤ የሰማያዊ ፓረቲ አባላትና ደጋፊዎች እነዲሁም ጋዜጠኞች ተገኝተዋል
እወነት ሁሌም ታሸንፋለች ሁሌም ከጎናችሁ ነን!!!!

Friday, March 14, 2014

በአሜሪካ የሚኖረው የሕወሐት ወንጀለኛ

ከኢየሩሳሌም አርአያ
The Ethiopian author, former TPLF torture czar and spymaster “Professor” Bisrat Amare
Bisrat Amare former head of TPLF Intelligence
የሕወሐት አባል የሆነውና በአሜሪካ የሚኖረው ብስራት አማረ በርካታ ወንጀሎችን እንደፈፀመ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ሕወሐት በረሃ እያለ የባዶ 6 እስር ቤት ዋና ሃላፊ የነበረው ብስራት አማረ የኢ.ህ.አ.ፓ አባላት የነበሩት እነ ፀጋዬ ገ/መድህን (ደብተራው) ጨምሮ በሕወሐት የተያዙትን በሙሉ ወረኢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በነበረ እስር ቤት በጅምላ አሰቃይቶ እንደገደላቸው ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎች « ኢዲዩና ፊውዳል..» በሚል ባዶ 6 ተብሎ ይጠራ በነበረው እስር ቤት ተሰቃይተው እንዲገደሉ የተደረጉት በብስራት አማረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ ከዚህ በተጨማሪ የድርጅቱን በርካታ አባላት እንዳስገደለ አያይዘው ገልፀዋል። እነተክሉ ሃዋዝ በዚህ ወንጀለኛ ከተገደሉት ይጠቀሳሉ ሲሉ ያክላሉ። በ1983ዓ.ም ሕወሐት/ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ የሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ምክትል የነበረው ብስራት አማረ ከቤተ መንግስት የጃንሆይ የነበረ ከፍተኛ ወርቅ በመዝረፍ መውሰዱን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚህ የዘረፋ ወንጀል ሆለታ እስር ቤት እንዲገባ መደረጉን ያመለክታሉ። በነስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ትእዛዝ እንዲፈታ ተደርጐ ወደ አሜሪካ የተሸኘው ብስራት አሜሪካ ሲጓዝ የዘረፈውን ወርቅ ይዞ እንደነበረ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች በግርምት ይገልፃሉ። ብስራት አማረ አሜሪካ ከመጣ በኋላ ቅርስ የሆኑትንና የዘረፋቸውን ወርቆች መሸጡንና አንዲት ሴት ለማሻሻጥ የተቀበለችውን 1ኪሎ ወርቅ ከወሰደች በኋላ እንደካደችው ማወቅ ተችሎዋል። ብስራት አማረ ስለዚሁ ጉዳይ ተበሳጭቶ የነገራቸው ምንጮች ማረጋገጫ ይሰጣሉ። የብስራት ታናሽ ወንድም የሆነውና በደህንነት ቢሮ ይሰራ የነበረው ታጋይ ጠስሚ (ጠስሚ -ትርጉሙ ቅቤ ማለት ነው) ከስራው በመልቀቅ የአስመጪና ላኪነት ትልቅ ቢዝነስ መክፈቱን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ ድርጅቱ የተከፈተው ብስራት አሜሪካ ከገባ በኋላ በላከለት ገንዘብ መሆኑን አስታውቀዋል። (ስለዚሁ ጉዳይ በ1995 ዓ.ም በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ መደረጉና የብስራት ወንድም ቅቤ ኢትኦጵ ቢሮ ድረስ በመምጣት የጋዜጣውን አዘጋጅ በድንጋጤ ተውጦ “የራሴን ቢዝነስ ተቋም ነው፤ እነማን መረጃ እንደሚሰጧችሁ አውቃለሁ። እባካችሁ የእኔንም፣ የወንድሜንም ስም አታንሱ?” በማለት ተማጽኖ አቅርቦ ነበር።) ብስራት አማረ ከሽማግሌው ስብሃት ነጋ ጋር ባለው የጠበቀ ግንኙነት ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለስ መቆየቱን ያወሱት ምንጮቹ፣ ወንጀለኛውና ዘራፊው መቀሌ ሄዶ አስገደ ገ/ስላሴን እንደከሰሰ አስታውቀዋል። የደርግ ወንጀለኞች ከአሜሪካ በገዢው ፓርቲ እየተወሰዱ ነገር ግን የኢ.ህ.አ.ፓ አባላትንና ሌሎች ንጹሃን ዜጎችን በጅምላ የፈጀና የአገር ቅርስ የዘረፈ ወንጀለኛ ጠያቂ ማጣቱ አስገራሚ ነው ብለዋል ምንጮቹ። ጠያቂ አካል ካለ በወንጀለኛው ብስራት አማረ ላይ ለመመስከር ፈቃደኛ መሆናቸውን አክለዋል። ይህን ምስክርነትና ማረጋገጫ ሊሰጡ የሚችሉና በአሜሪካ የሚኖሩ ሶስት የቀድሞ የሕወሐት ሹሞች እንዳሉና የብስራትን ወንጀል ጠንቅቀው የሚያውቁ መኖራቸውን አያይዘው ጠቁመዋል።

Thursday, March 13, 2014

ጠላቶቻችን መሳጂዶቻችንን ሲነጥቁን ጣራውንና ግድጊዳውን ብቻ ፈልገው እንዳይመስላችሁ ዋናው

አላማቸው እኛን ከ ኢባዳ (አምልኮ) ለማራቅ ነው፡፡
አማኞች ሆይ ኑ መሳጂዶቻችንን እንጠብቅ!
መሳጂዶቻች የህዝብ ደም ጠብታ ውጤቶች ናቸው...!!
Like ·  · 

አባ መላ ማን ነው? ጐፊር ነጩ ው

Frontline Club Oslo In the Name of Democracy: Land Grabbing and Genocid...

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ


የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ

march13/2014

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ውይይት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል ። የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባዘጋጁት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበዋል።
Karte Äthiopien englisch
መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንዲያሻሽል ያግዛሉ የተባሉ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል ። በስበሰባው ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ለተሰነዘሩት ወቀሳዎች የበኩላቸውን መልስ መስጠታቸው ተገልጿል ።በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮረው ውይይት ዛሬ የተደረገው ከ25,ተኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ። የውይይቱ ዓላማም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ዝርዝር ዘገባ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመጪው ግንቦት ከመቅረቡ አስቀድሞ ስለሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው ። ስበስባውን ካዘጋጁት ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች አንዱ መቀመጫውን ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ያደረገው ሲቪኩስ የተባለው ድርጅት የፖሊሲና የጥብቅና ጉዳዮች መኮንን ቶር ሆድንፌልድ ስብሰባው በተለይ በሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።


ከነዚህም እጎአ በ2009 ዓም የወጣው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ህግ አንዱ ነው ። ህጉ ከባድ ተፅዕኖ ማሳደሩና መዘዞቹም በውይይቱ መነሳታቸውን ሆድንፌልድ ገልፀዋል ። « በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት ለሚታገሉ ድርጅቶች በሚለገሰው ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ እርዳታ ላይ በተጣሉትን ገደቦች ላይ ተነጋገግረናል በዚህ ህግ ምክንያት በኢትዮጵያ ዓለም ኦቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አይሰሩም ። በርካታ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችም ከሰብዓዊ መብት ጋር የተገናኙ ሥራዎች ማካሄድ አቁመዋል ወይንም ከነጭራሹ ተዘግተዋል »
መድረኩ ትኩረት ሰጥቶ የተወያየበት ሌላው ጉዳይ ደግሞ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ ያደርጋል የተባለው ጫና ነበር ።
«ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተገቢው የህግ ሂደት ውጭ እንዲሁም በልዩ ደንቦች ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ የተጣሉትን ገደቦችም በውይይቱ ተነስተዋል ። በተለይ ስብሰባው በኢትዮጵያ 12 ጋዜጠኞች በቨረ ሽብሩ ህግ ምክንያት መከሰሰሳቸውኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የጋዜጠኝነት ተግባራቸውን ሲያከናውኑ ርዕዮት ዓለሙና እስክንድር ነጋ የመታሰራቸውም ጉዳይ ላይም ትኩረት ሰጥቶ ተነጋግሯል ።


ሆድንፌልድ እንደሚሉት በውይይቱ በኢትዮጵያ የነጻ ሚዲያ መገደብም ተነስቷል ። በጎርጎሮሳውያኑ 2012 5ጋዜጦች መዘጋታቸው በአሁኑ ሰዓትም ኢንተርኔ ት ከሚጠበቀው በላይ ቅድመ ምርመራ ይካሄድበታል ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃንንና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን የሚያነሱ ድረገፆች በኢትዮጵያ እንዳይሰሙና እንዳይታዩ በመንግሥት ይታገዳሉ ሲሉ ተወያዮቹ መገለፃቸውን ተናግረዋል ሆድንፌልድ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንያሽሽልም ሃሳቦች ተሰንዝረዋል ።
« 2009 ዓም የበጎ አድራጎት ና የሲቪክ ማህበራት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሰረዝ ወይም እንዲሻሻል ሁለተኛ የፀረ ሽብር ህግ በደል መፈፀሚያና ጋዜጠኖችን ማፈኛ እንዳይሆን እንዲሰረዝ በፀረ ሽብሩ ሕግ ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በሙሉ እንዲፈቱ እንዲሁም ተቃዋሚዎችና ሰላማዊ ሰልፈኞች ከሚቀጥለው ዓመት ምርጫ በፊት የመሰብሰብ መብታቸውን እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ሃሳብ ቀርቧል ።»
ዶቼቬለ ስለ ውይይቱ ና ስለተሰጡት አስተያየቶች የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮችን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። ሆኖም በውይይቱ ላይ የተካፈሉት የሰብዓዊ መብት ተመራማሪው አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም ያኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮችለመድረኩ የሰጡትን አስተያየት አጋርተውናል ።




Sunday, March 9, 2014

In the Name of Democracy: Land Grabbing and Genocide in Ethiopia



BY Nebiyou Alemayehu & Natnael kabtimer (oslo)
On 6th March 2014 Frontline club Oslo organized an event in collaboration with NEW FRONTIERS entitled “In the Name of Democracy: Land Grabbing and Genocide in Ethiopia” at Filmen Hus Oslo. As it is known Norway is the only Western country that has signed a bilateral agreement with the Ethiopian intelligence service facilitating forced return of refugees, even if the Ethiopian dictatorial government always receives strong international criticism for its gross human rights violations. In the event, four different individuals from similar and different point of view about Ethiopia and Ethiopians have been invited to present their standpoint about the current Ethiopian regime.
Abdullahi Hussein was the president’s adviser and head of the Ogaden TV channel Cakaara News. He had responded to the abuses and atrocities against civilians and for a few years he copied the president’s secret video files. Files included the internal meetings where individual officers and soldiers in the regional militia testify arbitrary arrests, torture, murder, extortion and rape. He presented unique video documentation revealing the dictatorship’s harsh treatment of its opposition, which he has smuggled out of the government and is taking to the International Criminal Court in The Hague. In general he has presented about the horrific circumstances in the Ogaden region, the handling of the evidence, and the process towards the International Criminal Court in The Hague.
DSC03366 (1)
The other presenter was Mr Obang Metho. He is a human rights activist who has tirelessly advocated for human rights, justice, freedom and environment, enhanced accountability in politics and peace in Africa for over 10 years. He has briefed leaders and officials at United Nations, the European Parliament, the US Department of State, the US Senate, the US House of Representatives, the World Bank and the Council for Foreign Relations, amongst others.
From Norway, Artist Solveig Syversen, who works with Ethiopian refugee status in Norway, has presented her work-in-progress documentary about the Norwegian-Ethiopian agreement of returning refugees.
The fourth person who presented his opinion about the current Ethiopian regime was, One Norwegian researcher from Bergen . His presentation was different from the other three in many ways and he seems to have a close relationship with the current Ethiopian regime. He presented verbal presentation in favor of the current Ethiopian regime specifically about the development of Ethiopia by referring the regime’s problems presented by Mr Hussien and Mr Metho as an “Exception”. His whole presentation has created great deal of disappointment in the audiences. He left at the middle of the event by avoiding questions from audiences.
video http://www.youtube.com/watch?v=5X8tbN6LLJ4

Saturday, March 8, 2014

አቶ ኦባንግ ሜቶ እና አቶ አብዱላሂ ሁሴን በኖርዌይ ኦስሎ ከኢትዮጵያውያንና ከኖርዌጅያን ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ

ው

አቶ ኦባንግ ሜቶ የአዲሲትዋ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ፓሬዝዳንትና አቶ አብዱላሂ ሁሴን  የኦጋዴን ክልል ፕሬዝዳንት አማካሪ የነበሩና በክልሉ የሚደረገውን የህዝብ ጭቆና፥ እንግልት፥ ግድያ  የሚያሳዪ ወደ መቶ ሰአታት የሚደርሱ የቪዲዮ ማስረጃዎችን ይዘው በመሰደድ ለአለም ህዝብ እያጋለጡ ያሉና በአሁኑ ሰአት በስዊድን ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት አጊንተው የሚኖሩ ሲሆን ከማርች 6 እስከ ማርች 7 ,2014 በነበራቸው የኖርዌይ ቆይታቸው ከተለያዩ የኖርዌይ ባለስልጣናት ጋር በሃገራችን ውስጥ ስለሚደረገው የሰብአዊ መብት ረገጣ በማስረጃ በተደገፈ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፥ በመቀጠልም በነበራቸው ቆይታ ስፖንሰር አድርገው ባመጧቸው Solveig Syversen በተባሉ አክቲቪስትና እንዲሁም  Frontline Club Oslo በተሰኘ ድርጅት በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኖርዌጂያንና ኢትዮጵያውያን Filmenshus በተባለ ቦታ ተገኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በማስረጃ በተደገፈ ለህዝብ ያቀረቡ ሲሆን ከታዳሚውም በተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፥ ማርች 7/2014 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አጋጣሚውን በመጠቀም በጠራው አስቸኴይ ስብሰባ አቶ ኦባን ሜቶ እና አቶ አብዱላሂ ሁሴን ከኢትዮጵያውያኑ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ያረጉ ሲሆን በቀጣይም በሃገራችን እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፥ ግድያ፥ እስራት ለማስቆም ምን መሰራት አለበት በሚሉት አንገብጋቢ ነጥቦች ዙሪያ ከታዳሚውም ከእንግዶቹም የተለያዩ ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ አቶ አብዱላሂ ሲያጠቃልሉ ያለብንን ችግር ለመፍታት የርስ በርስ ሽኩቻችንን ትተን ትኩረታችንን ሃገራችንን እያመሰ ያለው የወያኔ መንግስት ላይ እናርግ በማለት ምክራቸውን የለገሱ ሲሆን አቶ ኦባን በበኩላቸው እነዚህ በአቶ አብዱላሂ ሁሴን ከሃገር የወጡት ማስረጃዎች በጣም ተቃሚ ማስረጃዎቻችን እንደሆኑና ወደፊት ጊዜው ሲደርስ መጠየቅ ያለባቸው አካላት ሃላፊነት እንደሚወስዱበት ጠቁመው ነፃነታችንን ለማስመለስ ሁላችንም መታገል እንዳለብንና የውጩ አለም እኛን ነፃ ያወጣናል ብለን ዝም ብለን መቀመጥ እንደሌለብን ያሳሰቡ ሲሆን፥ በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ዋና ሊ/መ አቶ ዮሃንስ አለሙ ለታዳሚዎችንና ለእንግዶቹ  ምስጋና በማቅረብ በአጭር ግዜ በተጠራ የውይይት መድረክ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን መገኘታቸውን አድንቀው ለቀጣይ በጋራ ሊሰሩ ስለሚችሉ ስራዎች ግኑኝነት እንደሚቀጥልና ድርጅታቸውም በማንኛውም ስራ ላይ በግንባር ቀደምነት በሩን ከፍቶ እንደሚጠብቅ ገልፀው ስብሰባው ተጠናቋል፥፥
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

Friday, March 7, 2014

ኢትዮጵያዊው ከጎዳና ተዳዳሪነት ያወጡትን እናትና ልጅ ገድሎ ተሰወረ!


ዘጋቢ፦ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)
እናትና ህጻን ልጅዋን ገድሎ የተሰወረው ሰውዬ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በፈረንሳይ ፓሪስ ክርተማ የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ነበር:: ሟች ወ/ሮ ክውን ገዳሙ ትባላለች:: ከቤትዋ ወደ ስራ ቦታ ሲመላለሱ ተጠርጣሪውን የዩታል:: በጎዳናው የተጎሳቆለውን ሰው(ጉዳዩ በህግ ስለተያዘ ስሙን እዚህ ላይ አንጠቅሰውም) ስለሚያሳዝናቸው ባለፉ ባገደሙ ቁጥር እጃቸውን ይዘረጉለት ነበር::
ከግዜ በኋላ ከክረምቱ ብርድ እንዲገላገል ሲሉ ይህንን የጎዳና ተዳዳሪ ለግዜው በቤታቸው አስጠጉት:: የአቅማቸውን እየረዱት አብረው ለወራት ኖሩ::
ባለፈው ሳምንት አንድ አስደንጋጭ ክስተት በቤተሰቡ ውስጥ ተፈጸመ:: በችግሩ ያስጠጉት ሰው ከተኙበት በጭካኔ ገድሏቸው አመለጠ::
ወ/ሮ ክውን ገዳሙ የሶስት ልጆች እናት ሲሆኑ በፈረንሳይ ፓሪስ ለረጅም ግዜ ኖረዋል:: የሶስት ልጆች እናትም ናቸው:: ያለአባት ከሚያሳድጓቸውን ሶስት ልጆች ውስጥ አንደኛዋና የሁሉም ታናሽ ከሆነችው ጋር ላይመለሱ ይህችን አለም ባለፈው ሳምንት ተሰናበቱ::
ገዳዩ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በጩቤ ሰነጣትቆ ነው እናትና ልጅን ለህልፈት የዳረገው- እንደ ፈረንሳይ የዜና ምንጭ:: ባጎረሱት እጅ ተነከሱ:: ደግ ባደረጉ ምላሹ ግድያ ሆነ: ለዚያውም አረመኔያዊ ግድያ::
ነብሰ ገዳዩ ለግዜው ተሰውሯል:: የፈረንሳይ ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመሆን ጉዳዩን በጥብቅ ይዞታል:: እኛም እየተከታተልን ጉዳዩ ምን እንደደረሰ እናቀርብላችኋላን::

ብልጡ አልጀዚራ ኢቲቪን ሸወደው


በከበደ ካሳ
በኳታር መንግስት ሃብት የተቋቋመውና ስነ አፈጣጠሩ ሲጠናም የምዕራቡን አለምና የእስራኤል ሚዲያን የአረብ ሀገራት ጉዳይ አዘጋገብ ለመገዳደር የተፈጠረው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ስትራግል ኦቨር ናይል በሚል ርዕስ አንድ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅቶ ነበር። ጣቢያው ይህን ፊልም በቴሌቪዥኑ ያስተላለፈው ሲሆን በድረ ገፁ ላይ ስለጫነውም በርካቶች ተመልክተውታል።
የዘጋቢ ፊልሙ ይዘት በናይል ወንዝ የተነሳ በላይኛውና በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት መካከል ስለነገሰ ውጥረት ሲሆን ትኩረት ያደረገው ደግሞ ከላይኛው ተፋሰስ ኢትዮጵያ ላይ፤ ከታችኛው ተፋሰስ ደግሞ ግብፅ ላይ ነው። ይህን ፊልም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሞላ ጎደል እንደወረደ በሚባል ደረጃ ወደ አማርኛ ተርጉሞ አቅርቦታል። ‘ጠብቁን’ የሚል ማስታወቂያ መሰራቱና ፊልሙ በተደጋጋሚ መታየቱ የአባይ ፍጥጫ ከሚለው ጩኸታም ርዕሱ ጋር ተዳምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እንደተከታተሉት ለመገመት አይከብድም።
ይህን ዘጋቢ ፊልም የተከታተሉ የምቀርባቸውን ሰዎች ስለ ዘገባው ያላቸውን አስተያየት ጠይቄያቸው ነበር። የሚበዙቱ እንዳደነቁት ነግረውኛል። ሁሉም ለማለት በሚቻልበት ደረጃ በምስል አጠቃቀሙ፤ በትረካው ፍሰትና በታሪክ አወቃቀሩ በጥቅሉ በአቀራረብ ደረጃ ምርጥ የሚባል ዘጋቢ ፊልም እንደሆነ ይስማማሉ። እኔም በዚህ ረገድ ልዩነት የለኝም። ሆኖም አንዳንድ ያሳሰቡኝን ጥያቄዎች ሳነሳ የጠየቅኋቸውም እንደኔው ግር ይላቸዋል አለያም “እውነትክን ነው፤ ከኢትዮጵያ ጥቅምና አቋም ጋር ይጋጫል”ይሉኛል።
በእኔ እምነት ዘገባው ከኢትዮጵያ ይልቅ ለግብፅ ጥቅም ያደላ፤ ሶስተኛ ወገን ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለግብፅ እንዲጨነቅላት/እንዲያዝንላት የሚያደርግና ኢትዮጵያ ከምትከተለው አብሮ የመልማት ወይም በጋራ የመጠቀም እሳቤ ይልቅ ለፍጥጫና ግጭት መንስዔነት የቀረበ ነው። ይህን የምለው አልጀዚራ የአረብ አለም ሚዲያ ነው፤ ግብፅ ደግሞ የአረቡ አለም እምብርት ነች ከሚል አጠቃላይ ፍረጃ ተነስቼ ሳይሆን ከራሱ ከዘገባው ይዘት በመነሳት ነው። የማነሳቸው መከራከሪያዎችም በፊልሙ ውስጥ ቃል በቃል የሰፈሩ ናቸው።
ይህ ዘጋቢ ፊልም ለኢትዮጵያ አይበጅም ስል ምክንያት ከማደርጋቸው አንዱ የአባይ/ናይል ወንዝ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለግብፅ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አድርጎ ማቅረቡ ነው። እንደ ፊልሙ አባይ ለግብፅ የህልውና ጉዳይ ሲሆን ለኢትዮጵያ ግን የልማት ወይም የእድገት ጉዳይ ነው። በዘገባው ላይ እንደተገለፀው ካይሮ የተፈጠረችውና ያደገችው በናይል ወንዝ የተነሳ ነው። ያለ ናይል አካባቢው ሰው ሊኖርበት የማይችል በረሃ ነው። ማንኛውም ግብፃዊ በወንዙ ዙሪያ የመስፈር ፍቅሩም ከፍተኛ ነው። ስለሆነም “ሄሮዲተስ ግብፅን የአባይ ስጦታ ብሎ ገልጧታል። ትክክለኛ አገላለፅ ነው” ሲል ይደመድማል።
“በ1959ኙ ስምምነት መሰረት ግብፅ ከአባይ ወንዝ 55.5 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪውብ ውሃ ይደርሳታል። ሆኖም ግን ከዚያን ግዜ ጀምሮ የግብፅ ህዝብ በሶስት እጥፍ አድጎ 80 ሚሊዮን በመድረሱ የውሃ እጥረት አጋጥሟታል።” ተብሏል በፊልሙ ውስጥ። ቃለ ምልልሱ ያካተታቸው የግብፅ ወታደራዊ ተንታኝ “በህልውናና በደህንነት መካከል ልዩነት አለ፤ እኛ ሙሉ በሙሉ የአባይ ዉሃ ጥገኞች ነን። ሌላ የዉሃ ምንጭ የለንም። ስለዚህ ሃቁ ያለው በአባይ ዉሃ ላይ ስጋት የሚፈጥር ነገር ሲኖር በግብፆች ህልውና ላይ ያነጣጠረ ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ በእኛ ላይ የዉሃ ጥምና የሞት አደጋን እንዳያስከትል ያሰጋናል” ይላሉ።ስለተጠቃሚነት የተጠየቁት ኢትዮጵያዊ ወ/ሮ አጀበች ደግሞ በመብራት እጦት መሰቃየታቸውን ይናገራሉ። የነዚህ ንግግሮች ድምር አባይ/ናይል ለግብፃዉያን የህይወት ምንጭ፤ ለኢትዮጵያዉያን ግን የመብራት ምንጭ ነው የሚል ነው።
እኔ ወንዙ ለግብፅ በምን ያህል ደረጃ ያስፈልጋታል? የሚል ክርክር ውስጥ መግባት አልፈልግም። ወንዙ ከነሱ ህልውና ጋር አይተሳሰርም ብዬም አልከራከርም። ከግብፅ በላይ ለእኛ ያስፈልገናልም አልልም። ግን ሶስት ጥያቄዎችን አነሳለሁ።
አንደኛው ናይል ለግብፆች የሞት የሽረት ጉዳይ ስለመሆኑ ማውራቱ ለኢቲቪ ምን ይፈይድለታል? የሚል ነው። ይህንንማ ግብፃውያን ከውልደት እስከሞታቸው የሚሰበኩት አይደለም እንዴ። ይህንንማ በራሳቸው ሚዲያ ሁሌ የሚደጋግሙልን አይደል እንዴ? ትክክል አለመሆናቸውን ለማሳየት ነው እንዳልል እንዲያ የሚል ነገር አልሰማሁበትም።
ሁለተኛው ጥያቄዬ ምን የሚያሰጋ ነገር ስለመጣ ነው የግብፆችን ስጋት ማንፀባረቅ ያስፈለገበት? የሚል ነው። ኢትዮጵያ የዉሃው መጠን አይቀንስም፤ ማንም ሳይጎዳ ወንዙን በጋራ መጠቀም እንችላለን እያለች ባለችበት ሁኔታ የነሱን “በዉሃ ጥም እናልቃለን” ስጋት ማውራት ‘እንትን ያለበት ዝላይ አይችልም‘ እንደሚባለው አያስመስልምን? ይህ ነገር በተለይ ኢትዮጵያና ብሪታኒያ ወንዙን ግብፅን ለማንበርከክ ይጠቀሙበት ነበር ተብሎ ከቀረበው ታሪክ ጋር ሲዳመር የግብፅ ስጋት ተገቢ ነው ወደሚል ማደማደሚያ አያደርስም? በፊልሙ ውስጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ገዢዎች ከግብፅ ወርቅ ለማግኘት ሲሉ አባይን እንገድበዋለን እያሉ ያስፈራሩ እንደነበርና ብሪታኒያም የግብፆችን የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ ለመግታት ስትል በጥቁር አባይና በነጭ አባይ መካከል ግድብ መስራቷ ተመልክቷል። አልጀዚራ በተዘዋዋሪ እየተናገረ ያለው አሁንም ኢትዮጵያ ግድቡን ግብፅን ለማንበርከክ ልትጠቀምበት ትችላለች ነው።
ሶስተኛው ጥያቄዬ ሁለቱ ሀገሮች በፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ስምምነት ባልደረሱበት ሁኔታ ይህን ፊልም ያየ ሶስተኛ ወገን ምን ሊያስብ ይችላል? ነው። በፊልሙ ላይ ግብፆች ገና ከአሁኑ በዉሃ እጥረት እየተሰቃዩ እንደሆነ ለማሳየት ታስቦ የገቡ ምስሎች ብዙ ናቸው። በርካታ ግብፃውያን ጀሪካኖችን ይዘው በአንድ ቧንቧ ዙሪያ ሲራኮቱ ይታያሉ። ይህ ግን አጠቃላዩን የግብፅ ሁኔታ ገላጭ አይደለም። ይልቁንም ግብፆች የሚታወቁትና ራሳቸውም የማይክዱት በዉሃ አጠቃቀማቸው አባካኝ እንደሆኑ ነው። እንግዲህ ሶስተኛ ወገን ሲባል ለጋሽ ድርጅቶችን፤ ሃያላን መንግስታትን፤ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ያካትታል። ይህን ፊልም ሲመለከቱ የሚያዝኑት ለማን ይሆናል? መብራት ለምትፈልገውና ሌሎች አማራጮች አሏት ተብላ በፊልሙ ለተፈረጀችው ኢትዮጵያ? ወይስ ህይወቷ በሙሉ በናይል ላይ የተንጠለጠለና የመጠጥ ዉሃ አጥታ የምትሰቃይ ተደርጋ ለተሳለችው ግብፅ?
ሁለተኛው የመከራከሪያ ነጥቤ ዘጋቢ ፊልሙ አባይ/ናይልን ከትብብር ይልቅ የግጭት ምንጭ አድርጎ ስሎታል የሚል ነው። ይህን የምመዝነው ኢትዮጵያ ከያዘችው አባይ/ናይል የትብብር እንጂ የግጭት ምንጭ ሊሆን አይችልም ከሚለው አቋም ተነስቼ ነው። የዘጋቢ ፊልሙ ርዕስ በእንግሊዘኛው ስትራግል ኦቨር ናይል የሚል ሲሆን ኢቲቪ የተረጎመውም የአባይ ፍጥጫ በሚል ነው። የፊልሙ ችግር ከዚህ ይነሳል። የአልጀዚራን ቀልብ የሳበው ኢትዮጵያ የምትከተለው አባይ/ናይል ለሁላችንም በቂ ነው የሚለው የትብብር መንፈስ ሳይሆን ግብፅ የምትሰብከው የዜሮ ድምር ውጤት ነው። በግልፅም “ናይል የህይወትም የግጭትም ምንጭ ነው” ይላል። የህይወት ምንጭ የተባለው ለግብፅ ሲሆን የግጭት ምንጭ የተባለው ለሁለቱ ሀገራት መሆኑ ነው። የትብብር ምንጭ መሆን እንደሚችል ግን አያረጋግጥም።
ኢትዮጵያና ግብፅ ያላቸው ባላንጣነት እድሜ ጠገብ መሆኑን የሚገልፀው ይህ ፊልም ሁለቱም ሀገራት የስልጣኔ ምንጭ ከሆኑበት የጥንቱ ታሪካቸው ጀምሮ ተቀናቃኝ ሆነው መኖራቸውን ያሳያል። አፄ ኃይለስላሴ እና ገማል አብደል ናስር ሁለቱም ራሳቸውን የአፍሪካ ግንባር ቀደም መሪ አድርገው ስለሚወስዱ በያዟቸው ተቃራኒ የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት /ኢምፔሪያሊስትና ፀረ ኢምፔሪያሊስት/ ውስጥ ሆነው በተቀናቃኝነት መኖራቸውን ያትታል። ውጥረቱ በደርግ መንግስት ወቅትም መቀጠሉንና የዚህም ምንጩ መንግስቱ ኃይለማርያም ፊቱን ወደ ሶቪየት ሲያዞር አንዋር ሳዳት ደግሞ ወደ ምዕራባውያን በማዞሩ ሁለቱ ሀገሮች በሁለቱ የአለም ጎራዎች ማዶና ማዶ መሰለፋቸው እንደሆነ ያስታውሳል። አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ አስቸጋሪ ፈተና ውስጥ ገብታለች ይላል የአልጀዚራው ጋዜጠኛ።እንደዘገባው “አሁን ኢትዮጵያ በሁለት አማራጮች የተወጠረች ሀገር ሆናለች። በአንድ በኩል ወንዙን ለልማት የማዋል በሌላ በኩል ደግሞ ከታችኞቹ የአባይ ተፋሰስ ጎረቤቶቿ ጋር ያላትን ግንኙነት በማሻከር መካከል ያሉትን አማራጮች በትኩረት ታያቸዋለች።”
እዚህም ላይ ዘገባው እውነትን አልያዘም ብዬ አልከራከርም። ጥያቄዬ ይህ እውነት ትብብርን በምንሻው በእኛ በኢትዮጵያውያን መዘገቡ ፋይዳው ምንድን ነው? የሚል ነው። የኔ ጥያቄ ለምን ያለፉትን የግጭት መንስዔዎቻችንን ከምናጎላ አዳዲሶቹን የትብብር አማራጮቻችንን አንተነትንም? የሚል ነው። አሁን አፄዎቹ የሉም፤ ደርግም ተገርስሷል። በምትኩ ያለው‘በጠላቶች ተከብቤያለሁ’ ከሚል የቆየ ስሜት ራሱን አውጥቶ ከጎረቤቶቹ ጋር በጥቅም የተሳሰረ፤ ይህንንም ወደ ሌላ ታላቅ ምዕራፍ ለማሸጋገር እየሰራ ያለ መንግስት ነው። ታዲያ ፊልሙ ምነዋ ይህን ተግባራችንን ዘነጋው? ምነውስ ከጎረቤቶቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት ሳናሻክር አብረን መበልፀግ ይቻላል የሚለውን ሶስተኛውን አማራጭ ሳያቀርበው አለፈ?
ወደ ሶስተኛው ምክንያቴ ልለፍ። በዚህ ዘጋቢ ፊልም ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዱ ነገር ግን በአግባቡ ምላሽ ያልተሰጠባቸው ሃሳቦች አሉ። አንደኛው ግብፃዊው የፖለቲካ ተንታኝ አብዱል ዋሂብ ያነሱት ሃሳብ ነው። “የቀድሞ ስምምነቶችን ማክበር አለብን። ይህ ለአለም አቀፋዊ የሀገራት ድንበርም የሚያገለግል አካሄድ ነው። ለምሳሌ ከነፃነት በፊት የነበሩ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ድንበሮችን መቀየር አንችልም። እነዚህ በቅኝ ገዢዎች የተከለሉ ድንበሮች ከነፃነትም በኃላ ህጋዊ ሆነው እንዲያገለግሉ ከስምምነት ተደርሷል። ስለዚህ በአባይ ዉሃ አጠቃቀም ዙሪያ የተፈረሙትንም ስምምነቶች በተመሳሳይ መልኩ ማየት ነው።” ይላሉ። የ1929ኙን ስምምነት መሆኑ ነው። ጋዜጠኛው ደግሞ “የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ግን እነኚህ ስምምነቶች የቅኝ ግዛት ቅሪት ስለሆኑ ተቀባይነት የላቸውም ሲሉ ይከራከራሉ” ይላል።
የኢትዮጵያ መከራከሪያ ግን ይህ ሊሆን አይችልም። የስምምነቱ አካል ስላልሆንኩ ለመቀበል የሚያስገድደኝ ምንም አይነት ህግ የለም ነው የምትለው ኢትዮጵያ። የቅኝ ግዛት ቅሪት በሚለው ከሆነማ አብዱል ዋሂብ እንዳሉት የድንበር ማካለሉን ተቀብለን ስምምነቶቹን እንቢ የምንልበት ምክንያት አይኖርም። አልጀዚራ ይህ ጠፍቶት ሳይሆን ኢትዮጵያ የያዘችውን ትክክለኛና ምክንያታዊ አቋም አለባብሶ ለማለፍ ስለፈለገ ነው።
በሌላ መልኩ “በአለም አቀፉ ህግ መሰረት የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ግድብ ከመስራታቸው በፊት የታችኞቹን ተፋሰስ ሀገራት የማማከር ግዴታ ስላለባቸው ለግብፅ ማሳወቅ አለባቸው” ይላሉ። ይህም እንደ ሃቅ ተቀባይነት አግኝቶ ያለፈ ነው በዘጋቢ ፊልሙ። እውነታው ግን ይህን አይነት አስገዳጅ አለም አቀፍ ህግ ያለመኖሩ ነው። ይልቁንም ህጉ የሀገራትን ሉዓላዊ መብት የሚያከብርና ፍትሃዊና በሌላው ላይ ትርጉም ያለው ጉዳት ያለማድረስ መርሆችን የሚያበረታታ መሆኑ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ1997 ያወጣው ለመጓጓዣነት የማያገለግሉ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም ስምምነት እኩል/ሚዛናዊ ተጠቃሚነትና ከፍተኛ ጉዳት ያለማድረስን ነው መሰረት የሚያደርገው። እኩል/ሚዛናዊ ተጠቃሚነት ደግሞ የህዝብ ብዛትን፤ የቆዳ ስፋትን፤ ሊታረስ የሚችል መሬትን፤ ሌሎች አማራጭ ምንጮችንና የዉሃውን ደህንነት መጠበቅ የሚባሉ ጉዳዮችን ያቀፈ ነው። ስትራግል ኦቨር ናይል ግን እነዚህን ጉዳዮች ዘወር ብሎ አላያቸውም።
ሌላው ግብፆች የሚመኩበትና እስካሁንም አወዛጋቢ የሆነው በአፄ ሚኒሊክና በብሪታኒያ መንግስት መካከል ተፈርሟል የሚባለው ስምምነት ነው። ይህንን የግብፆችን መከራከሪያ ነጥብ ሳያስተባብሉ እንደወረደ ከማቅረብ በላይ የኢቲቪን ወገንተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ጉዳይ አይኖርም። ፊልሙ ላይ እንዲህ ይላል። እንግሊዝ እ.አ.አ በወርሃ ግንቦት 1902 ከአፄ ሚኒሊክ ጋር አንድ ስምምነት ተፈራረመች። በዚህ ስምምነት አፄ ሚኒሊክ የአባይ ወንዝ ወደ ግብፅ የሚያደርገውን ፍሰት የሚያሰናክል ወይም የዉሃውን መጠን የሚቀንስ ምንም አይነት ግድብ እንደማይገነቡ ቃል ገቡ።” የሚገርመው በቅርቡ በናይል ቲቪ በተካሄደ የቀጥታ ስርጭት ውይይት ላይም የቀድሞው የግብፅ የዉሃ ሚኒስትር ዶ/ር ናስር አደም ይችን ነጥብ አንስተዋታል።
አፄ ሚኒሊክ ፈርመውታል የተባለው ስምምነት ፕሮፌሰር አሊ አብዱላህ አሊ እንደሚሉት ቢያንስ በሁለት መሰረታዊ ነጥቦች የተነሳ በአሁኑ ወቅት ተቀባይነት የለውም። አንደኛ ስምምነቱን የሁለቱ ሀገራት የወቅቱ የዘውድ ም/ቤቶች አላፀደቁትም። ሁለተኛ የስምምነቱ የአማርኛና የእንግሊዝኛ ትርጉም ግጭት ፈጥሮ ስለነበር አፄ ሚኒሊክ በወቅቱ አልተቀበሉትም። አልጀዚራ ያዘጋጀውና ኢቲቪ የተቀበለው ዘጋቢ ፊልም ይህንን የግብፅን የክስ ነጥብ ያሳይና የኢትዮጵያን መከራከሪያ ነጥብ ግን አያስቀምጥም። በዚህም በህግ የመርታት አዝማሚያው ለግብፅ ያጋደለ እንዲመስል አድርጓል።
የመጨረሻውን ነጥቤን ላንሳ። እንደፊልሙ ከሆነ የኢትዮጵያን የአፈር ማዕድን ጠራርጎ የሚሄደው ደለል ለግብፃዊያን ሲሳያቸው ነው። ፊልሙ “ለም አፈር ለግብፃውያን ዋና ስጦታ ነው” ይልና ምክንያቱን ሲያብራራ መሬታቸው በለም አፈር ይበለፅግላቸውና አጥጋቢ ምርት ያገኛሉ ይላል። ይህን ከተቀበልን ኢትዮጵያ ‘ግድቤ ደለልን በመቀነስ የታችኞቹን ሀገራት ተጠቃሚ ያደርጋል’ የምትለው ድለላ /lip service/ ነው ማለት ነው። አልጀዚራ ይህን ይበል እንጂ እውነታው ግን እሱ አይደለም። ግብፅ የአስዋን ግድብን ከገነባች በኋላ ደለሉ በግድቡ የታችኛው ክፍል ላይ ስለሚተኛ ተጠቃሚ ሳይሆን ተጎጂ ነው የነበረችው። ስለዚህም የኢትዮጵያ አቋም ትክክል ተብሎ ነበር መወሰድ ያለበት።
ልብ በሉ፤ አሁን ልክ አይደለም የምለደው አልጀዚራን አይደለም፤ ኢቲቪን ነው። አልጀዚራማ ከሚዲያው ጥቅም ተነስቶ የሚፈልገውን መልዕክት አቅርቧል። እኔ የምተቸው የኢትዮጵያ የሆነውን ኢቲቪን ነው። ዘገባው ከላይ ያስቀመጥኳቸው የይዘት ጉድለቶች ሳሉበት ለምን ኢቲቪ አስተላለፈው? ነው የኔ ጥያቄ። ለአንድ ደቂቃ ማስታወቂያ በሺዎች የሚቆጠር ብር የሚቀበለው ኢቲቪ ለምን የአየር ሰዓቱን በዚህ ማቃጠል አስፈለገው? ነው የእኔ ጥያቄ። የኢትዮጵያን ጥቅም ማስጠበቅ የሚችል የፀዳ ዘጋቢ ፊልም በውስጡ ባለው የዶክመንታሪ ክፍል መስራት የሚችለው ኢቲቪ ለምን የአልጀዚራን ዥጉርጉር ፊልም መኮረጅ አስፈለገው? ነው የኔ ጥያቄ።
እያንዳንዱ ሚዲያ ሲቋቋም የራሱ ተልዕኮ ይዞ ነው። ለጥቅሙ የሚቆምለት ወገንም አለው። አልጀዚራ የኳታርን ብሔራዊ ጥቅም በሚጎዳ ተግባር ውስጥ እጁን አያስገባም። በአንፃሩ የኳታርን ሲያልፍ ደግሞ የአረቡን አለም አጀንዳዎች ከፍ ከፍ አድርጎ ያሰማል። ኢቲቪ የሚከተለው የሚዲያ ፍልስፍና ልማታዊ ጋዜጠኝነት ነው። በልማታዊ ዴሞክራሲ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ውስጥ እንደመሆኑ በተለይ እንደ ኢቲቪ ያለ የህዝብ ሚዲያ ግልፅ ተልዕኮዎችን ይዞ መንቀሳቀሱ የማይቀር ነው። እናም የኢትዮጵያን ሕዳሴ ማብሰር ዋና ተልዕኮው ነው።
ሁለቱ ተቋሞች በተልዕኮም በሚከተሉት ፍልስፍናም የማይታረቁ ባህሪዎች አሏቸው። ኢቲቪ ከአልጀዚራ ያገኘውን ዘገባ እንደወረደ ለአድማጭ ተመልካቹ የሚዘረግፍ ከሆነ ተሸውዷል ማለት ነው። አሁንም የሚታየኝ ይሄው ነው። ግድ የላችሁም፤ አልጀዚራ በውብ ምስሎቹና በማራኪ አቀራረቡ የተነሳ ኢቲቪን ሸውዶታል። ግን ለሌላ ግዜ ትምህርት ይሆነዋል ብዬ አስባለሁ።

Thursday, March 6, 2014

በመንግስት ታጣቂው በጥይት ተደብድበው የተገደሉት ባልና ሚስት ፎቶ ተገኘ


Be Hiwehat tataki
እብሪተኛ የመንግስት ታጣቂዎች ለሚቀጥፉት የሰው ህይወት መንግስት ተጠያቂ የሚሆነው መቼ ነው?ከዳዊት ሰለሞን
የመንግስት ታጣቂዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ደማቸው በትንሽ በትልቁ እየፈላ ሲቪል ዜጎችን የሚጨርሱበት አጋጣሚ ከቀን ቀን እየጨመረ ነው፡፡
የባህር ዳሩን ዘግናኝ እልቂት ለጥቆ ቂርቆስ ቤ/ክ አካባቢ ሁለት ሰዎችን በጥይት በመምታት የወሲብ ደምበኛው እንደነበረች የተነገረላትን ሴት ሲገድል አብሯት የነበረውን ማቁሰሉ አይዘነጋም፡፡የታክሲ ሹፌሩ አልጭንህም ስላለው የታጠቀውን ሽጉጥ በመምዘዝ ለፍቶ አዳሪውን በአጭር አስቀርቶታል፣አራት ኪሎ ቤተ መንግስት አቅራቢያ በሚሄድ መኪና የተርከፈከፈ ጥይት ስንቱን እንዳስቀረ እግዜር ይወቀው ፡፡በየአካባቢው እንዲህ አይነት ዘግናኝ ዜናዎችን መስማት አዲስ አይደለም፡፡
ከትናንት በስቲያ በላፍቶ ክፍለ ከተማ አቦ ማዞሪያ አካባቢ በምስሉ የምትመለከቷቸውን የሶስት ልጆች ወላጆች እብሪተኛው ታጣቂ በጥይት በመደብደብ ገድሏቸዋል፡፡ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡እሰየው ነው ፡፡ግን በቃ?እነዚያን ሶስት ህጻናት ማን ነው የሚያሳድጋቸው?ግለሰቡን አምኖ ክላሽ ያስታጠቀው አካል የማይጠየቀውስ እስከመቼ ነው?
መንግስት የመኪና አሽከርካሪዎች የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ እንዲገቡ እያስገደደ መሆኑ በመኪኖቹ አደጋ ለሚደርስበት ሰው አንዳች ነገር ነውና ይበረታታል፡፡መንግስት በነካ እጁ የሚያስታጥቃቸው ሰዎች ለሚያደርሱት የመብት ጥሰት ኢንሹራንስ ይግባ!!!በእኔ እምነት ስለ ተገደሉት ወላጆችና ወላጅ አልባ ስለሆኑት ልጆች መጮህ የሁላችንም ግዴታ ነው።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ.


ALEMYEHU ATOMSSA
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድርና የኦህዴድ የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ።
አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ45 አመታቸው ነው ዛሬ ለሊት ሰባት ሰዓት ላይ ያረፉት።
አቶ አለማየሁ ከየካቲት 9 ቀን 2006 ጀምሮ በባንኮክ ህክምናቸውን ሲከታተሉ እንደቆዩ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።
በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው አቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓ.ም ነው የተወለዱት አቶ አለማየሁ።
የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫም ፥ ላለፉት 24 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ እና መላው የአገሪቱ ህዝቦች ዛሬ ለደረሱበት የሰላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ተጠቃሚነት እንዲበቁ በቁርጠኝነት የታገሉ ነባር ታጋይ ነበሩ ብሏል።
በ1981 ዓመተ ምህረት የደርግን ስርዓት ለመገርሰስ ሲካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ተቀላቅለዋል።
ከ1988 እስከ 1994 ድረስም የኦህዴድ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት እና የድርጅቱ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ በመሆን አገልግለዋል።
ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የኦህዴድ ሊቀመንበር ሆነው ፥ ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ደግሞ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ሰርተዋል። 

Breaking news

Mimi Sebhatu, Zami radio host talking about ESAT

Tuesday, March 4, 2014

የአላሙዲ የሃብት ደረጃ ከዓለም ቢሊየነሮች እድገት አሳየ፤ የዓለማችን 61ኛው ቢሊየነር ሆኑ

ታዋቂው የዓለማችን የቢዝነስ መጽሔት ፎርብስ በየዓመቱ የዓለማችንን ቢሊየነሮች ደረጃ የሚያሳውቅበትን መረጃ ይፋ አደረገ። ባለፈው ዓመት የዓለማችን ሁለተኛው ሃብታም የነበሩት የማይክሮሶፍት ባለቤት ቢል ጌትስ የዓለማችን አንደኛ ቢሊየነር ሲሆኑ የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከምበርግ 21ኛው የዓለማችን ቢሊየነር ሆኗል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በመሬት ነጠቃ የሚከሰሱት ሼህ መሀመድ አላሙዲ የዓለማችን የሃብታምነት ደረጃቸው ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ አምና ከነበሩበት የ65ኛ ደረጃ 4 ደረጃዎችን በማሻሻል የዓለማችን 61ኛው ሃብታም ሆነው በመጽሔቱ ተቀምጠዋል። እንደ ፎርብስ ገለጻ የ8 ልጆች አባት የሆኑት በአባታቸው የሳዑዲ፤ በእናታቸው ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሆኑት አላሙዲ $15.3 ቢሊዮን አላቸው።
ከሳዑዲ አረቢያ ሃብታሞች መካከል ሁለተኛው የሆኑት አላሙዲ የወያኔ/ኢሕአዴግ ደጋፊ ከመሆናቸውም በላይ፤ ከስር ዓቱ ጋር በፈጠሩት ስር የሰደደ ወዳጅነት በአድልዎ አብዛኛው የኢትዮጵያ ወሳኝ የንግድ ተቋማት በርሳቸው ስር እንዲያዙ ትልቅ ውለታ እንደተዋለላቸው በተደጋጋሚ እንደሚተቹ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። ምንም እንኳ ሼኩ በነዳጅ ዘይት ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ቢሆኑም በተለይም የኢትዮጵያን ወርቅ በእርሳቸው ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የሰውዬው ሃብት ከእለት ወደ ዕለት እንዲጨምር አስችሎታል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።
የፕላኔታችን 10ሩ ቢሊነሮች የሚከተሉት ናቸው።
1ኛ. ቢል ጌትስ 76 ቢሊዮን ዶላር
2ኛ. ቻርሎስ ሳሊም ሄሉ 72 ቢሊዮን ዶላር
3ኛ. አማሪኮ ኦርቴጋ 64 ቢሊዮን ዶላር
4ኛ. ዋረን ብፌት 58.2 ቢሊዮን ዶላር
5ኛ. ላሪ ኤልሰን 48 ቢሊዮን ዶላር
6ኛ. ቻርለስ ኮች 40 ቢሊዮን ዶላር
7ኛ. ዳቪድ ኮች 40 ቢሊዮን ዶላር
8ኛ. ሼልደን አንደርሰን 38 ቢሊዮን ዶላር
9ኛ. ክርስቲ ዋልተን እና ቤተሰቦቿ 36.7 ቢሊዮን ዶላር
10ኛ. ጂም ዋልተን 34. 7 ቢሊዮን ዶላር
የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በ28.5 ቢሊዮን ዶላር 21ኛ፣ አላሙዲ በ15.3 ቢሊዮን ዶላር 61ኛ፣ ቸልሲ ስፖርት ክለብ ባለቤት ኢብራሞቪች በ9.2 ቢሊዮን ዶላር 137ኛ ሆነዋል።
zehabesha

‹‹730 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት›› የተሰኘው አዲሱ ዘጋቢ ፊልም ይፋ ሆነ!

ድምፃችን ይሰማ
‪#‎EthioMuslims‬ ‪#‎730DaysforReligiousFreedom‬
‹‹730 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት›› የተሰኘው አዲሱ ዘጋቢ ፊልም ይፋ ሆነ!
ሰኞ የካቲት 24/2006

የትግላችንን ሁለተኛ አመት ለማሰብ ከሳምንታት በፊት ለ15 ቀናት ባካሄድነው የዘመቻ ፕሮግራም ታቅደው ከነበሩ ስራዎች አንዱ የሁለቱን አመት ትግላችንን በመጠኑ የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም ማዘጋጀት እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከሰሞኑም ፊልሙ በቅርብ ቀን ይፋ የሚሆን መሆኑ ተገልጾ የፕሮቫ ማስታወቂያ መለቀቁ አይዘነጋም፡፡

እስካሁን በተለያዩ ምክንያቶች በመዘግየቱ ይቅርታ እየጠየቅን ‹‹730 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት›› የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም በዛሬው እለት ይፋ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን! እንደተለመደው ፊልሙን ላልደረሳቸው እንዲደርስ የማድረጉን ሃላፊነት እንደህዝብ ተረባርበን መሸከም እንደሚኖርብን ሳናስታውስ አናልፍም!

የዘጋቢ ፊልሙ ሊንክ፡-

http://www.youtube.com/watch?v=heZkMThP2hQ&feature=youtu.be

ትግላችን እስከድል ደጃፍ ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

አስቸኳይ የቤት ስራ ለሁላችንም ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthioMuslims‬



የሚከተሉት መረጃዎች ለአስቸኳይ ስራ የሚፈለጉ በመሆናቸው ሁሉም ሙስሊም በእጁ የሚገኙትን መረጃዎች በማካፈል የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ሊወጣ ይገባል፡፡

1. አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በየአካባቢያችን ባሉ መስጂዶች የተደረጉ የሰደቃና አንድነት ፕሮግራሞችን ሲዘጋጁ መግቢያ በር ላይ የተሰቀሉ የነበሩ የመስጂዱን ስም እና የደሰቃ ፕሮግራሙን ማስታወቂያ የያዘውን ባነር በፎቶ

2. በተለያዩ አካባቢዎች መንግስት አንድነት እና የሰደቃውን ፕሮግራም ለማጨናፈግ ካደረገው ተግባራት መካከል በፎቶ የተነሱትን በተለይ መንግስት ክልከላ ሲያደርግ ፣ መንገድ ሲዘጋና ድንኳኖችን ሲያፈርስ እና |የመሳሰሉትን የሚያሳዩ ፎቶዎች ፣

3. የሰደቃና አንድነት ፕሮግራሞችን ለማስታወቅ የተበተኑ የጥሪ ወረቀቶች ፣ ደብዳቤዎችና ማስታወቂያዎችን በፎቶ ማሰባሰብ ፣

4. ሀምሌ 6 የነበረውን ክስተት ( ድብደባዎችና ጭፍጨፋዎችን የሚያሳዩ) ፎቶግራፎች ፣

5. የመንግስትን ጣልቃ ገብነት የሚያሳዩ የምስጂድ መታሸግ፣ፕሮግራም እገዳ፣ ዳዕዋ ክልከላ እና የመሳሰሉትን የያዘ ደብዳቤዎች ፈልገን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በዘመቻ መልክ ከላይ የተተቀሱትን መረጃዎች አሰበስበን እንድንልካቸው በአላህ ስም እንጠይቃለን ፡፡ ማንኛውም ሙስሊም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን እና በእጁ የሚገኙትን ፎቶዎች እና ዶክመንቶች ለመሰብሰብ እንዲያመች በቅርብ ለምናገኛቸው የፌስቡክ አክቲቪስቶች እና ከዚህ ቀጥሎ በተገለፁት ኢስላማዊ ፔጆች ላይ በመላክ |የበኩላችንን ሃላፊነት እንወጣ፡፡

በFree Our Heroes፣ Furaat Orgrat፣ ፈስቢር፣ Ethio Bilal Tube፣ FITH RADIO [ፍትህ ሬዲዮ]፣ BBN ቢቢኤን የናንተው ድምፅ፣ እንዲሁም መሰል ፔጆች ላይ ቢላኩ በቀላሉ መሰብሰብ ይቻላል ፡፡
ለምታደርጉት ትብብር ሁሉ አላህ ምንዳችሁን ይክፈላችሁ ድል ለሙስሊሙ !
አላሁ አክበር !