በአገራችን ኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት በደርግ ዘመን ከተፈፀሙትም የከፉ ወንጀሎችን በሰብአዊ ፍጥረታት ላይ እየፈፀመ ነው፡፡ ደርግ በተኮሱበት ላይ ተኩሷል፤ በኢሕአፓ ላይም ቀይ ሽብር በማወጅ ብዙ ወጣቶችን ጨፍጭፏል፡፡ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በሰብአዊ ፍጥረታት ላይ የተፈፀሙና እየተፈፀሙ ያሉት ዘግናኝ ግፎች ኢሕአዴግ በምኑም ከደርግ ያልተለየ፣ እንዲያውም ደርግ የፈፀመውን ቀይ ሽብር በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከመፈፀም ወደኋላ የማይል ከደርግም የከፋ ፍፁም አረመኔ መንግሥት መሆኑን ነው በግልጽ የሚያመላክቱት፡፡ ስለዚህም በኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ውስጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው …
- ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ስብሃት ነጋ፣ ደብረጽዮን፣ ሽፈራው ተክለማርያም፣ ሙሉጌታ ዉለታው፣ ሽመልስ ከማል፣ ሬድዋን ሑሴን፣ እና ሌሎችም የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት፣
- የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
- ‹‹ማዕከላዊ›› በሚባለው የሰው በላ አውሬዎች መናኸሪያ ያለማንም ከልካይ የሰው ልጅን በማሰቃየት የዕለት ከዕለት ተግባር ላይ የተሠማሩ አውሬዎች እና ኃላፊዎቻቸው በሙሉ …
- የኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት የደኅንነት ኃላፊ፣
- የኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ዋና አቃቤ ሕግ፣
- የኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት የፍትኅ ሚኒስትር፣
- የማሰቃየት ወንጀል የተፈፀመባቸውን ዜጎች በ‹‹ሽብርተኝነት›› የሚወነጅል ዶኩመንታሪ እያቀናበረ የኢትዮጵያ ህዝብን በማታለል በሰብአዊ ፍጥረት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎችን የሕጋዊነት ቀለም ለመቀባት የሚተጋው የፌደራል ፖሊስ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል አባላት፣
- በቅጥፈት የዶኩመንታሪ ቅንብሩ ላይ እጃቸው ያለበት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባልደረቦችና የመንግሥት ደኅንነት ሠራተኞች …. በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሰብአዊ ፍጥረት ላይ ወንጀል በመፈፀም፣ እንዲፈፀም በማዘዝ እና በመፍቀድ፣ በሰብአዊ ፍጥረት ላይ ወንጀል ሲፈፀም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በመተባበር የወንጀል ክስ ሊመሠረትባቸው ይገባል፡፡
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
No comments:
Post a Comment