Wednesday, April 16, 2014

በቤኒሻንጉል ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በፈፀሙት ጥቃት የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ




በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ተሸከርካሪ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ።
የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ለፋና በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፤ ማንነታቸው ያልተወቀ ሰዎች በተሽከርካሪው ላይ ጥቃቱን ያደረሱት ማክሰኞ ከንጋቱ 12 ሰዓት ተኩል ላይ ነው ።
ጥቃቱ የተፈጸመው ከአሶሳ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሸርቆሌ ወረዳ ልዩ ስሙ ጠይባ በተባለው ሥፍራ ነው ።
በወንጀል ድርጊቱ ዘጠኝ ሰዎች ሲገደሉ በሌሎች ስድስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ወንጀሉን ፈጽመው የተሰወሩት ግለሰቦችን አድኖ ሕግ ፊት ለማቅረብ የፀጥታ ኃይሎች ክትትል በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
በወንጀሉ ተጠያቂ የሆኑት ግለሰቦች ማንነት ለማጣራትም የወንጀል ምርመራ ሥራ መጀመሩና የምርመራ ውጤቱን የሚመለከቱ መረጃዎችም በወቅቱ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረጉ ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.)

No comments:

Post a Comment