Sunday, April 27, 2014
Wednesday, April 23, 2014
"ሱሪህን አውልቅ" አለኝ። "እኔ ወንድ ነኝ፡፡ ወንድ ፊት ሱሪዬን አላወልቅም። ወንድ የወንድን ገላ ለማየት አይጓጓም፡፡
....ወድያው ከፀሀይ መሞቅ እንደገባሁ 49 ቁጥር ቢሮ ለምርመራ ተጠራሁ፤ በካቴና ታስሬ ነበር የመጣሁት። አለማየሁ፣ "መርማሪ ይለወጥልኝ ትላለህ አለ? ምን አይነት መርማሪ ነው የምትፈገው?" አለኝ። ዝም አልኩት።
"ሱሪህን አውልቅ" አለኝ።
"ሱሪህን አውልቅ" አለኝ።
"እኔ ወንድ ነኝ፡፡ ወንድ ፊት ሱሪዬን አላወልቅም። ወንድ የወንድን ገላ ለማየት አይጓጓም፡፡ ሱሪዬን አላወልቅም። ከፈለግክ አውልቀው" ስለው ደህንነቱ ተናዶ ምራቁን ተፍቶብኝ በቦክስ ሆዴን አለው። የሥነ ልቦና ጫና ስለደረኩበት ሱሪዬን ሳያወልቅ ቀረ። ኢንስፔክተር ዓለማየሁ ተቀብሎ ፂሜን ሲነጭ አስጮኸኝ። "ዝም በል!" ብሎ ጉሮሮዬን ሲያንቀኝ ትንፋሽ አጥሮኝ ዝም አልኩ። ፊት ለፊት ታስሮ የነበረውን ካቴና ፈትቶ ወደኋላ አሰረኝ። ደህንነቱ ቀድሞ ፂሜን እየነጨ በስክሪብቶ ጫፍ ጠቀጠቀኝ።
"ይህ ሆ ያለው ህዝብ ነገ ዞር ብሎ አያይህም! አንተንም ህዝብህንም እናስተነፍሳችኋለን። አሁን ራስህን ብታወጣ ይሻላሀል" እጄ ወደኋላ በመታሰሩ ፊቴ ላይ ተገትሮ እስክሪብቶውን የአይኔ ብረት ጋር እያደረሰ አሳቀቀኝ፡፡ አፍንጫዬ ውስጥ ከትቶ ስቃዬን አብዝቶታል።
እሱ ስልክ ተደውልሎት ሲወጣ ኢንስፔክተር አለማየሁ ተቀበለኝ። መሬት ጣለኝ። "ተንበርክከህ ሂድ" አለኝ ። በቅጣት ጫና "የበፊት ጉዳቴ እየተሰማኝ ነው፣ ዛሬን አሳርፈኝ" አልኩት። አልተባበረኝም። አልዘነለኝም። መሬት አንከባሎ ረግጦኝ ትቶኝ ቁጭ ብሎ መጽሔት ያነብ ጀመር።
በመሐል"ተነስ ቁጭ በል" አለኝ። ሁለት እጅ ወደ ኋላ ታስሮ ራስን ችሎ ከመሬት መነሳት ከባድ ነው፤ በተለይ ለደከመ ፆመኛ። ግድግዳ ተደግፌ ተነሳሁ። "ወንበር ላይ ተቀመጥ" አለኝ። ተቀመጥኩ። የሚያነበውን "የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሔት" ጠረጴዛ ላይ አመቻችቶ አስቀምጦ "አንብብ" አለኝ። "በሀገሪቱ የስራ ቋንቋ ነው የተፃፈው፤ ለምን አንተ አታነበውም?" አልኩት። በጥፊ መታኝ፡፡ በራሱ ምልክት ሰጠኝ "አንብብ" የሚል፡፡ "ነፃ ሀሳብ" በሚል አምድ ስር የተፃፈ ነው። ፀሀፊው እኔ ራሴ ነኝ። "ሰላም ሲበዛ ራስ ያማል እንዴ?" በሚል ርዕስ ስር የተፃፈ ነው፡፡ ፍቶ ግራፋም የኢ-ሜይሌ አድራሻዬም በግልጽ ተቀምጧል። ለረጅም ደቂቃ ሳነበው ቆይቼ "ድምጽህን ከፍ አድርግ" ብሎ እያነበብኩ እያለ ድንገት ከኋላዬ ጆሮ ግንዴን የሚያላጋ ጥፊ ነፍሴን አሳተው። እነሆ ዛሬ ድረስ የግራ ጆሮዬ ለበሽታ ተዳርጓል። በወቅቱም ማዕከላዊ በሚገኘው ክሊኒክ ባደረግኩት ምርመራ "ጆሮህ ቁስለት አለው" የሚል ምላሽ ተሰጥቶኛል። በአወደደቄ ጎኔ ከፍተኛ መቀጥቀጥ ገጥሞኝ ስለነበር መታሻና መርፌ ተወግቻለሁ።
ጀግናው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው ያቀረበው የክስ መከላከያ
ይቀጥላል…..
Tuesday, April 22, 2014
BBN ቢቢኤን የናንተው ድምፅ በሲዊዲን ታላቅ የአንድነት እና የዱአ ፕሮግራም ተካሄደ ቢቢኤን ፡- በሲዊዲን የሚገኙ ኢትዪጲያውያን በትላንትናው እለትና በዛሬው እለት ታላቅ ፕሮግራም አካሄደዋል፡፡ ከደቡብ አፍሪካ ተነስተው በጀርመን
በተካሄደው ፕሮግራም ላይ ጣፋጭ የዳእው ስራቸውን
ያቀረቡት ሸኅ ሙሃመድ ሀሚዲን ወደ ስዊድን ከተማ
አቅነተዋል፡፡ ወደ ሲዊዲንም ባመሩበት ጊዜ አቀባበል
የተደረገላቸው ሲሆን እሳቸውም ምንም እረፍት ሳያደረጉ
ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አንድነትን አስመልክቶ ዳእዋ
አድረገዋል
በሲዊድኑ ፕሮግራም ላይ ሌላም ታላቅ አሊም ተሳታፊ
ነበሩ፡፡ የአወልያ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የነበሩት
ዶክተር አብደላ ከድርም ፕሮግራሙን አድምቀውታል፡፡
ፍትህ ያጡ ኢትዪጲያውያንም ፍትህን ያገኙ ነስርም ይመጣ
ዘንድ ዱአ ተደርግዋል፡፡ ኡስታዝ ሙክታርም ከለንደን
የፕሮግራሙ ተሳታፊ እንደነበሩ ለማወቅ ተችልዋል፡፡
ከሀገር ማዶ የሚገኙ ኢትዪጲያዊያን በጋራ በመሰባሰብና
በመተሳሰብ የዲን ትምህርታቸውን ከመማማር ባሻገር
በሀገር ቤት ያለውን ትግል ለመደገፍ አንድነታቸውን
እየገለፁ ይገኛሉ bbn
Subscribe to:
Posts (Atom)