Thursday, December 20, 2012

የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ የተሳካ እና ውጤታማ ለማድረግ በ አንድነት ተነስተናል


ሰላም ወገኖች
እኛ  በኖርዎይ የምንገኝ የኢትዮጵያ ስደተኞች ሃገራችን የሚገኘውን ዘረኛ ፣ አፋኝ እና አምባገነን መንግስት  በመቃዎም  ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች እያደረግን እንገኛለን ። ከነዚህ እንቅስቃሴዎች መካከል አንዱ የኢትዮጵያን  ህዝብ እውነተኛ የሆነ መረጃ እንዲያገኝ ፤ በሃገር ወዳድ የኢትዮጵያ ዜጎች የተቋቋመውን  ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን(ኢሳት)  መርዳት ነው ።


እንደምናውቀው ተራራውን አንቀጠቀጠን የሚሉትን የማፊያ ቡድን ወያኔን ፤ ኢሳት እውነት ለኢትዮጵያን  ህዝብ በማቀበል ብቻ እያንቀጠቀጣቸው ይገኛል ። ኢሳት የኢትዮጵያን  ብቸኛ ህዝብ አይን እና ጆሮ  ብቸኛ ሳይሆን በተግባርም አንደበት ስለሆነ  Feb 10-2013  በ ኖርዎይ ዋና ከተማ በኦስሎ  ይካሄዳል ። በዚህ ቀን ሃገር ወዳድ ወንድማችን ታማኙ  አርቲስት ታማኝ በየነ  ተጋባዥ እንግዳችን  ነው ። ለኢሳት ፣ ለአርቲስት ታማኝ በየነ  እንዲሁም ለኢትዮጵያን ህዝብ ክብር ስንል  በስደት የምንኖርበት ሃገር የሚደረገውን የገቢ ማሰባሰቢያ የተሳካ  እና ውጤታማ ለማድረግ በ አንድነት ተነስተናል ።

 በዚህ አጋጣሚ  በኖርዎይ የምትገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያ ወዳጆች በዚህ ዝግጅት በመገኘት  ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን (ኢሳት) ለሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ የራስዎን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በክብር ጋብዘንዎታል ።


ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ  !!!
ሞት ለውያኔ እና ሆድ አደሮች !!!

No comments:

Post a Comment